Sunday, May 14, 2017

የሲኖዶሱ ውግዘት መፍትሔ አያመጣምቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ የተቋቋመችው የክርስቶስን ወንጌል በመስበክ በእርሱ የማዳን ሥራ የሚያምነውን ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዲገባ ለማገልገል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ስትመሰረት ከዚህ የተለየ ዓላማ የላትም፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ዓላማዋን ከዘነጋችና መንገዷን ከሳተች ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ይህን በመገንዘብ ወደ ቀደመው የወንጌል እውነት ተመልሳ በክርስቶስ ኢየሱስ መዳን የሚገኝበትን ወንጌል እንድትሰብክ ለማድረግ የተንቀሳቀሱትን የገዛ ልጆቿን ሥርዓቱን ተከትላ፣ አነጋግራና የንስሐ ዕድል ሰጥታ፣ ሳይሆን አቅርባ ሳታነጋግር አውግዣለሁ ለይቻለሁ ስትል ኖራለች፡፡ በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ራሱ ከሳሽ ራሱ ምስክርና በእጅ አዙር ራሱ ዳኛ በሆነው ማኅበረ ቅዱሳን በኩል ልዩ ልዩ ስም በመስጠት ህገ ወጥ ውግዘቱን ገፍታበታለች፡፡ ይህን በማድረጓ ግን ከኪሳራ በቀር ያገኘችው ጥቅም የለም፡፡ እንዲያማ ቢሆን ኖሮ ከዚህ ቀደም ባስተላለፈችው ሕገ ወጥ ውግዘት የወንጌልን እንቅስቃሴ ማዳፈን በቻለች ነበር፡፡ ነገር ግን ሲያወግዙትና እናስቁምህ ሲሉት የሚብሰውና ይበልጥ የሚቀጣጠለው የወንጌል እንቅስቃሴ በአስገራሚ ሁኔታ በየቦታው እየጠቀጣጠለ ይገኛል፡፡ ሕገ ወጥ ውግዘትም አያስቆመውም፡፡
ማኅበረ ቅዱሳንም ሆነ አሁን ያለው የእርሱ ጉዳይ ፈጻሚ የሆነው ሲኖዶስ አላስተዋሉትም እንጂ እያወገዙ ያሉት የወንጌልን እንቅስቃሴ ነው፡፡ በሌላ ምንገድ እየተጣሉ ያሉት ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ እንዲሰበክ ካዘዘው ጌታ ጋር ነው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ውግዘት ያስተላለፈው በክርስቶስ ቀጥሎም በሐዋርያት የተሰበከውን ወንጌል በማጣመም ሌላ ወንጌል በሚያስተምሩት ላይ ነው፡፡ በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ። ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።” (ገላትያ 1፡6-9)፡፡ ዛሬ እየሆነ ያለው ግን ተገላቢጦሹ ነው፡፡ እውነተኛውን የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩት ይወገዛሉ፡፡ እውነተኛውን ወንጌል የሚያጣምሙና ሌላ ባዕድ ወንጌል የሚሰብኩት ደግሞ ያወግዛሉ፡፡ በእርግጥ ይህን መለወጥ አይቻልም የወንጌል ባሕሪ ይህ ነውና፡፡   


በአበው ዘመንም የነበረው ውግዘት በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት ላይ ጥርጥርና ክሕደት ያመጡትን ሰዎች የተመለከተ ነበር፡፡ ይኸውም በዋናነት በምስጢረ ሥላሴና በምስጢረ ሥጋዌ ላይ ኑፋቄና ክሕደት ያመጡትን ሰዎች ጉባኤ ሰብስቦ ተከራክሮና ረትቶ፣ የንስሐ ዕድልም ሰጥቶ በዚህ ዕድል አልጠቀምም በያዝኩት አቋም እጸናለሁ የሚለውን ነበር ከአንድነታቸው የሚለዩት፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ግን በምስጢረ ስላሴም ሆነ በምስጢረ ሥጋዌ ላይ ያሻቸውን እየተናገሩ ብዙ ኑፋቄና ክሕደት ያመጡት ሰዎች በተገቢው መንገድ መወገዝ ሲገባቸው ማንም አልነካቸውም፡፡ ከዚህ በተቃራኒው የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩትን ግን ወንጌልን በመስበካቸውና ሌሎች የስሕተት ትምህርቶችን በመቃወማቸው እየወገዙ ይገኛሉ፡፡
ድርጊቱን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ውግዘቱ ወደ ሲኖዶስ መቅረብ ሳያስፈልገው ሃይማኖታዊ ጉዳይን የመመለከት አቅምም ብቃትም በሌላቸው የበታች አካላት ጭምር እንዲካሄድ መፈቀዱ ነገሩን ተራ አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም የሃይማኖት ሕጸጽ የሌለበትን ሰው ሁሉ ማንም እየጠነሳ በግል ቂምና በቀል ልዩ ልዩ ስም በመስጠትና የሐሠት ክስ በማቀነባበር ያሹትን የማውገዝ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የበላይ አካል የሆነው ሲኖዶስም ጉዳዩን በአግባቡ ከመመርመር ይልቅ የቀረበለትን ውግዘት በማጽደቅ የቤተ ክርስቲያኗን ውድቀት የሚያፋጥን ተግባር እየፈጸመ ይገኛል፡፡                     
ቀድሞ ቤተ ክርስቲያኒቱን ይመሩ የነበሩ በዕውቀትም በልምድም በዕድሜም የበሰሉ አባቶች ነበሩ፡፡ አሁን ግን ከአንዳንድ ጥቂት አስተዋይና ዕውቀቱ ያላቸው አባቶች በቀር አብዛኞቹ ጳጳሳት በዕውቀታቸውና በቅድስናቸው ተመስክሮላቸው ሳይሆን በወገንተኝነትና በጉቦ ጭምር ወደ ጵጵስና የመጡ በመሆናቸው ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለግል ጥቅማቸውና ምስጢራቸውን ይዞ የሚፈልገውን እንዲፈጽሙለት ለሚያስፈራራቸው ማኅበር ሐሳብ አስፈጻሚ የሆኑ በመሆናቸው አባቶች ተመሪ፣ ማኅበሩ ደግሞ መሪ የሆነበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም እየተከናወነ ያለው ማህበሩ የሚለው ነውና፡፡ ውግዘትም እንዲህ ቀልሎ የሚገኘውና የልጆች ጨዋታ የመሰለው መሪና ተመሪው ቦታ ስለተለዋወጡ ነው፡፡ በዚህ ምንገድ የተጀመረው ጉዞ ቤተክርስቲያኒቱን ወደ ጥፋት የሚወስድ እንጂ መፍትሔ የሚያመጣላት አይደለም፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ በተገቢው መንገድ አቅርባና አነጋግራ፣ መክራና ዘክራ፣ የንሥሀ እድልም ሰጥታ ሳይሆን በየጊዜው ጉዳዩ በሚመለከታቸውም በማይመለከታቸውም ክፍሎች እንዲያው በማውገዝ ብዙ የደከመችባቸውንና በቀላሉ የማትተካቸውን ሊቃውንት፣ መምህራን፣ መነኮሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ መሪጌቶችና ምእመናን እያጣች ነው፡፡ ተገቢውን ትኩረት ሰጥታ ባለመጠበቅና ባለመመገብ፣ ዘመኑን በዋጀ አገልግሎት መያዝ ባለመቻሏና በሌሎችም ምክንያቶች የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ባለበት ሁኔታ የእርሷ ግን እየቀነሰ መሄዱ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ለፍልሰቱ ተጠናክሮ መቀጠል በሌሎች ከማላከክ ይልቅ እራሷ እያደረገች ያለው ፍሬቢስ ውግዘትና ከላይ የተዘረዘሩት ደካማ አገልግሎቷ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረጉን ማመን አለባት፡፡   
ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የሚናገረው ልሳኖቿም በየጊዜው የሚመሰክሩት ቤተ ክርስቲያኒቱ ትልቅ አደጋ ውስጥ መሆኗን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሁኔታዎችን ተመልክቶ የወደፊቱን ከመተለም ይልቅ ፍልሰቱን የሚያባብሱ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎችንና ምድር ላይ ያለውን እውነታ ከመቀበልና ቤተ ክርስቲያኗን ከመታደግ ይልቅ፣ ራሳቸውን ብቻ በማድመጥ ምንም እንዳልተፈጠረ የሚቆጥሩ አባቶች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ መሬት ያለው እውነታ ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው፡፡ ለዚህ መፍትሔው ደግሞ ምንም አይመጣም ጠንካራ ነን ብሎ ባሉበት መርገጥ ሳይሆን ምን እናድርግ ብሎ ትክክለኛውን መፍትሄ ለመፈለግ መነሳት ነው፡፡ ዋናዎቹ ጥያቄዎች እኛ በየጊዜው እያወገዝንና እያባረርን ችግሩ የቀጠለውና የምእመናን ፍልሰት በአስደንጋጭ ሁኔታ እያሻቀበ ያለው ለምንድነው? ከዚህ ቀደም የወሰድነው መፍትሔ ውግዘት የሚሠራ ነው ወይስ ሌላ መፍትሔ መፈለግ አለብን? ወዘተ… መሆን አለባቸው፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ ልሳን የሆነው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በጥርና በየካቲት 2009 እትሙ “ምንደኞች ወይስ ባለቤቶች?” በሚል ርእስ ባሰፈረው ርእሰ አንቀጽ ቤተ ክርስቲያኗ ላይ ትልቅ አደጋ መጋረጡን በተጨባጭ ማስረጃዎች ጠቁሟል፡፡ የሚዲያን ጥቆማ ተቀብሎ መጠቀም የአባቶች ፋንታ ነበር እነርሱ ግን ያን ያነበቡትም አይመሰልም፡፡ ቢያነቡትም ከቁብ አልቆጠሩትምና አደጋውን የሚያባብሱ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው፡፡ ቁጥሩ እያሻቀበ ካለው የኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል 45 ሚሊዮኑ የቤተክርስቲያኗ አባል መሆኑን የጠቆመው ርእሰ አንቀጹ ቀሪውን ሕዝብ ሌሎች የእምነት አራማጆች እንደተካፈሉት ገልጿል፡፡ “ከሁሉም የሚያሳዝነው ፀረ ክርስትና አቋም ባላቸው ወገኖች ተማርኮ የተወሰደው ሕዝብ ነው፡፡ ግማሹም ወደሌላ እምነት እንዲሄድ የተገደደው በድህነቱ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ መቼም ቤተ ክርስቲያን ልትጠየቅበት አትችልም፡፡” ብሏል፡፡
በፀረ ክርስትና ክፍሎች የተወሰደው ሕዝብ የሚያሳዝን መሆኑ በእርግጥም ትክክል ነው፡፡ ወደሌላ እምነት የሄደው በድህነቱ ምክንያት ነው የሚለው ግን የሞኝ ዘፈን ነው የሚሆነው፡፡ “በዚህ መቼም ቤተ ክርስቲያኒቱ ልትጠየቅበት አትችልም” የሚለው አነጋገርም አስተዛዛቢ ነው፡፡ ሕዝቡን ያደኸየው ማነው? ለሕዝቡ የአስተሳሰብና የአኗኗር ኋላቀርነት ምክንያት ይቆጠር ቢባል በዋናነትና በመጀመሪያ ደረጃ የምትጠቀሰው ቤተክርስቲያኗ ናት፡፡ ሌላው ቀርቶ ሕዝቡ ሠርቶ እንዳይለወጥ በደነገገችው የበዓላት ብዛት ጠፍራ አስራ ሕዝቡን ለድህነት ዳርጋው አልኖረችም ብሎ አለመመስከር ሐሰተኛ ያሰኛል፡፡ ስለዚህ ወደሌሎች እየፈለሰ ያለበት ዋናው ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሕዝቡ የሚመጥን ነገር ባለማቅረቧና ሕዝቡን በአግባቡ መያዝ ባለመቻሏ፣ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ መስሕብነት ባላቸውና ዘመኑን በዋጁ አገልግሎቶች መሳብ በመቻላቸውና ለሕዝቡ የነፍስ ጥያቄ ምላሽ የሚሆን ነገር እያቀረቡ በመሆናቸው ነው ማለት ይቻላል፡፡
ይህን ሐቅ በግልባጩ ያመለከተው ርእሰ አንቀጹ “አርባ አምስት ሚሊዮኑ የእምነቱ ተከታዮችም ቢሆኑ አብዛኛዎቹ ትምህርት አግኝተው ያመኑ ሳይሆኑ ‘የእናት አባታችንን እምነት አንለቅም’ በማለት በልማድና በስማ በለው እንዲሁ ያመኑ ናቸው፡፡” ብሏል፡፡ ስለዚህ የሄደው ብቻ ሳይሆን የቀረውም አስተማማኝ በሆነ ምክንያት በእምነቱ ውስጥ እንደሌለና ነገ እርሱም ላለመፍለሱና የአባላቷ ቁጥር ከዚህ በባሰ ሁኔታ ላለመመናመኑ ምንም ማስተማመኛ እንደሌለ ግልጽ ነው፡፡ ርእሰ አንቀጹ ሲቀጥል ጊዜው በሰጠው ምቹ ሁኔታ ሌሎቹ የእምነት ድርጅቶች አባላቶቻቸውን ለማብዛት እየጠሯሯጡ መሆናቸውን ጠቅሶ “የእኛ ብቃት ማጣትና ስንፍና መንገዱን ምቹ ያደርገላቸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ነባሮቹ የእምነታችን ተከታዮች ልጆቻቸውን በእግራቸው ሳይተኩ በሞትና በእርግና እየተገባደዱ ነው፡፡ እኛ ግን በቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ የ80 ዓመት አዛውንቶችና አሮጊቶች ሲያንዣብቡ እየተመለከትንና በየበዓለ ንግሡ ጥቂት የሰንበት ተማሪዎች የሚያሰሙትን ድምፀ ዝማሬ በመስማት ብቻ ትውልዱ ከእኛ ጋር ያለ እየመሰለን ለደረሰብን ከፍተኛ አደጋ ትኩረት አልሰጠነውም፡፡ ዜማውም፥ ቅኔውም፥ ግጥም ገጣሚ፥ ዘማሪና ዘፋኝ ከመደቀል ያለፈ በእምነት የተገነባ ትውልድና ራሱ አምኖ ሌላውን ለማሳመን የሚችል ሰባኬ ወንጌል ሊያፈራልን አልቻለም፡፡” በማለት ያንዣበበባትን አደጋ ገና መመልከት አለመጀመሯን ጠቁሟል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ሲኖዶሱ በትክክለኛው አቅጣጫ መነጋገር መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ውሳኔን መወሰንና ተግባራዊ ማድረግ አልቻለም፡፡ በተደጋጋሚ እንደታየው ሲኖዶስ ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች ይልቅ በአስተዳደራዊና እጅግ ተራ በሆኑ ግለሰባዊ ጉዳዮች ጭምር ተጠምዶ ነው ጥቅምትንና ግንቦትን የሚያሳልፈው፡፡ ርእሰ አንቀጹ ከዚህ ጋር በተያያዘም ያለው ነገር አለ “የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካላትም አብዛኛውን ጊዜ  በግብረ ሙስና የተካሰሱ የአህጉረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎችንና ሰራተኞችን፥ የአድባራት አለቆችንና ካህናትን የዳኝነት ሥራ ሲሰሩ ነው የሚውሉት፡፡ ‘ስብከተ ወንጌል ተጓደለ አገልግሎት ታጎለ፥ እምነታችን በመጤ እምነት ተበከለ አባላችን ኮበለለ የተከታዮቻችን ቁጥር ወደ ታች አሽቆለቆለ’ በማለት ለአቤቱታ ወደ በላይ አካል የሚመጣ አካል ግን የለም፡፡ የግብረ ሙስናው ጉዳይማ ከአንዳንድ የበላይ አካላትም ጋር የተዛመደ በመሆኑ  የዳኝነቱም ሥራ በቶሎ እልባት ሊያገኝ አልቻለም፡፡” ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካላት ብዙ የቤት ሥራቸውን ሳይሰሩና በቀጣዩ ትውልድ የምትቀጥል ቤተ ክርስቲያንን በተገቢው መንገድ ሳያቆዩ በእንቅርት ላይ … እንዲሉ ውግዘት ማስተላለፋቸው ምን ይሉታል? ውግዘቱ መፍትሔ ያመጣ ይሆን ወይስ ችግሯን ያባብሰው ይሆን? የሚለውን ዕድሜ ከሰጠን አብረን የምናየው ይሆናል፡፡
በትክክል ከታየ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት መሰረት ከጳጳሳቱ ጀምሮ መወገዝና ከሹመታቸው መሻር የሚገባቸው ብዙዎች እያሉ እነርሱ ምንም ሳይባሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አውቀው ወደ ትክክለኛው የመዳን ምንገድ እንዲመጡ ወንጌል የሰበኩትና እንታረም ያሉትን እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች አለስማቸው ስም በመስጠት “መናፍቅ” እያሉ ማውገዝ ራስን በራስ ከማጥፋት ተለይቶ አይታይም፡፡ በቅርቡ በአባ ሳዊሮስ ሀገረ ስብከት እንዲሁም ሰሞኑን በተካሄደው የሲኖዶስ ስብሰባ የተላለፈው ውግዘት ተወጋዦችን የሚጎዳ አይደለም፡፡ የወንጌል እንቅስቃሴውንም የሚገታ አይደለም፡፡ እንዲያውም ይበልጥ ያጋግለዋል፡፡ ውግዘቱ የመጣው የወንጌሉ እንቅስቃሴ እያሸነፈ በመሄዱ ነውና ለእንቅስቃሴው ሕያውነትና እግዚአብሔር በሥራ ላይ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በውግዘት የቆመና የተሰናከለ የወንጌል እንቅስቃሴ በታሪክ የለም፡፡ እንዲያውም ውግዘት ለአገልግሎቱ አዲስ አቅጣጫ በማሳየትና ሰዎችን ይበልጥ ለወንጌል ሥራ እንዲጨክኑ በማድረግ የወንጌልን ሩጫ ያፋጥናል፡፡ ወንጌል በውግዘት የሚቆም ቢሆንማ ኖሮ በ2004 የተካሄደው ውግዘት ውጤት አምጥቶ ሌሎችም ያንን በማየት ተቀጥተው ራሳቸውን በማረም ቤተ ክህነቱ እንደሚፈልገው ይጓዙ ነበር፡፡ ነገር ግን ወንጌል በምንም ሁኔታ ተቃውሞና ውግዘት ቢገጥመው መሄዱ ይቀጥላል እንጂ አይቆምም፡፡ ሌላው ቀርቶ አሳዳጁ ሳውል ተሰዳጁ ጳውሎስ ሆኖ መለወጡን መዘንጋት የለብንም፡፡    
በመጨረሻም አንድ ልብ መባል ያለበት ጉዳይ አለ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮቿንም ሆነ ምእመናኖቿን የያዘችበት ምንገድ የፍቅርና ተገቢውን የምጋቤና የኖላዊነት ሥራ በመሥራት ሳይሆን በማስፈራራትና በማስገደድ ነው፡፡ ብዙው አገልጋይ ባለፉት ዓመታት በወንጌል የተገለጠውን የመዳን መንገድ የመረዳት እድል እንዳገኘ ሁኔታዎች ይመሰክራሉ፡፡ ነገር ግን ይህን የወንጌል እውነት በነጻነት እንዳይመሰክርና ምእመናን በእምነታቸው ጸንተው በወንጌልም እውነት አርፈው በቤተ ክርስቲያናቸው ጸንተው እንዲኖሩ እንዳያደርግ ከእንጀራው የማፈናቀል አደጋ ከፊቱ ተጋርጦበታል፡፡ ምእመናንንም በወንጌል ስብከት ሳይሆን የቀብር ቦታና አንዳንድ አገልግሎቶችን አታገኙም በማለት በማስገደድ የመያዝ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ይህ ዘመን ተሻጋሪ መፍትሔ አይደለም፡፡ እንዲያውም እነዚህ ሁኔታዎች ውሎ አድሮ የሚያመጡት ውጤት የከፋ ነው የሚሆነው፡፡ በዚህ ምንገድ ሰዎችን ለመያዝ መሞከር ብዙ አዋጭ አይደለምና ቤተ ክርስቲያኒቱ ቆም ብላ ራሷን መመርመር ይኖርባታል፡፡  

20 comments:

 1. MK IS SO POOR TO UNDERSTAND Z PROBLEM

  ReplyDelete
  Replies
  1. Think ten times before u talking about mk because ur living for eating.

   Delete
 2. "ሐዋርያው ጳውሎስ ውግዘት ያስተላለፈው በክርስቶስ ቀጥሎም በሐዋርያት የተሰበከውን ወንጌል በማጣመም ሌላ ወንጌል በሚያስተምሩት ላይ ነው፡፡ " ብለሃል ጥሩ ነው:: ስለዚ የአሰግድ ሳህሉ መወገዝም ትክክል ማለት ነው ፣ምክንያቱም ሰውዬው ወንጌልን አጣሞ እየተረጎመ ኢየሱስ አማላጅ ነው በማለት አስተምሯል::

  ReplyDelete
 3. leloch ga silemin tikelawutalachihu. Malazenun akumeh erasihin mermir

  ReplyDelete
 4. ጥፋቱ ምንድነው ተጠርቶ ተጠይቋል ወይ በመለኮት ባህሪ ላይ ያለተገባ ነገር ተናግሯል ወይ???????በጭራሽ ወንጌል መስበክ ሰውን የሚያሰወግዝበት የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ልጆችዋን እንደ ድመት ወልዳ የምትበላ ስንት መልካም ነገር እንዳላት ሁሉ ስንት ቆሻሻ መፅሀፍትን በጉያዋ አቅፋ የሙጥኝ ያለች አውጋዦችዋም ፀረ ወንጌሎች ክብራቸው ክርስቶስ ሳይሆን ገንዘብ የሆኑ ለመንጋው የማይራሩ መወገዝ ተገቢ ቢሆን የሚወገዘው ሌላ ነበረ።በቅናት በምቀኝነት በተንኮል ተነሳስተው ነው ሁሉን የሚያደርጉ።ደግነቱ ውግዘታቸው ከተሰበሰቡበት አዳራሽ ጣሪያ አያልፍም።እላይ እኮ የሉም ደስስስስ የሚለው እነሱ አይደሉም መንግስተ ሰማያት የሚያስገቡ መንገዱም በሩም ቁልፉም እርሱ እየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ።ወንጌል ይሰበካል ወንጌልን የማያሰብኩም የማይሰብኩም በወንጌሉ የሚያፍሩ ከስም ሁሉ በላይ ለሆነው እየሱስ የሚለውን ስም የሚጠሉ የሚያፍሩበትም ሁሉ በቃሉ መሰረት የተረገሙ እነሱ ይሁኑ።ዘመድኩን የምትባለው ሰው እንደዚህ በገንዘብ ተገዝተህ አንዱን ስትረግም ስትሰድብ ስም ስትሰጥ ገንዘብ ሲከፈልህ ስም ስታድስ እንዲህ ሆነህ ባመጣኸው ገንዘብ የሚያድጉት ልጆችህ ቤተሰብህ ያሳዝናሉ የደም ገንዘብ።ለነገሩ የቤተክርስቲያንዋ ምእመን ደንበኘ ማሳያ ምሳሌ ነህ በስድብ የሰለጠንክ ያሰለጠንክ እግዚዎ ።እግዚአብሄር የለም የሚሉት እንኳ እዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራውን ግፍ ደፍረው አይሰሩም።ለማኘውም በታችኛ ው እንጂ ላይ ቤት ስለሌላችሁ ውግዘታችሁ ከንቱ ነው።

  ReplyDelete
 5. በእስር ቤት ተዘግቶ ወንጌል አይከደን
  ሰንሰለቱ እስኪወድቅ እርሱን እንሰብካለን
  የዝምታ ቀን የለነም
  ሳንመሰክር አንሞትም።

  ReplyDelete
 6. ወንድም የምትለዉ ሁሉ ያንተን መሰሪነት የሚገልፅ እና ከቻልክ እንድትመለስ ልትጠቀምበት ይገባል፡፡ለነገሩ ይህን የቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ያዘመተህ ትንቢት የተነገረለት ታላቁ ዘንዶ በመሆኑ የርሱም መንገድ ጠራጊ በመሆንህ መመለሱ ፈተና ሊሆንብህ ይችላልና አልቅሰህ ተፀፅተህ እግዚአብሄርን ሃይልንና ጉልበት እንዲሆንህ ተማፅነህ ንስሃ ግባ? አይሻልህም? በዚህ ዘመን ሆነህ ቤተክርስቲያን ከጥንት ጀምራ ስትሰብከዉ የኖረችዉን ወንጌል ተሳስቷል እያልክ አዲስ ወንጌል ለመስበክስ የምትሞክር አንተ የጥፋት ሰዉ ነህ፡፡ባትሰማኝም ልንገርህ፡፡ብዙዎች በጥበባቸዉ ጠፍተዋል፡፡መፃፍ ቻልኩ ብለህ ሁኔታዎች ተሳኩልኝ ብለህ ለጥፋት ባትዘምትስ ምናለ?ለምን አገልግሎትህ የእዉነት ከሆነ ጭራሽ ክርስትና የማያዉቁትን ወገኖች በአደባባይ አትሰብክም?ምክንያቱም ቅድስት ቤተክርስቲያን ዛሬም ወንጌሉን ትሰብካለች የጌታን ልደቱን ተወለደልን ብላ ሞቱን ትንሳኤዉን ሁሉ ከመዳናችን ጋር አያይዛ መሰረቷ ስለሁነ እየሰበከች ነዉ፡፡እየመረረህም ቢሆን ይህን እዉነት ተጋት፡፡ከዚህ እዉነት የወጡት ላይ ለምን አትሰራም?ሲጀመር ጠላት ምንጊዜም ጦሩን የሚሰብቀዉ እዉነት ላይ ነዉ በጌታችንም የተደረገዉን አይተናልና፡፡

  ReplyDelete
 7. bete kirstian kibruan tebika yemitadergewun enkskase enadenkalen. ahunm mefafikan meleyet alebachew. yihm beki aydelem.

  ReplyDelete
 8. Yeazagn qibe anguach!! Bsmen wollo hgrsebket yalut tamariachhu - merigeta ferie sibhat "belto meqedes ychalal" belew simekru tderesebachew!! Tawqobachihual!!

  ReplyDelete
 9. tehadisowoch lemin yerasachihun church(bete christian alalkum) atimeseritum? woim pentewoch adarash atihedum lemin yegnan bet tibetebitalachihu.leba yimesil masmesel sirachihu new lemin badebabay eminetachihun atigeltsum?

  ReplyDelete
 10. አልተወገአም እኮ ሰዎች ከሳሾች ሰው ምን ነካው ግን ክርስቶስ የደም ዋጋ የከፈለለትን ሰው ይወገዝ ይገደል ይሰቀል ማለት?????ልክ ፀሀፍት እና ፈሪሳውያንን ነው የምንመስል የዲያቢሎስ ልጆች በመክሰስ የተወቁ ናቸው።ማህበረ መናፍቃን።ሸቀጣሞች ወንጌል ካልተደበላለቀ ደስስ የማይላቸው።

  ReplyDelete
 11. ግን ዘመድኩን የሚባለው ሰውዬ እናትየው ከሰይጣን ጋር ተጋብተው ነው እንዴ የወለዱት????ከሰው መቼም እንዲህ አይነት ሰው አይወለድም ።ዲኤንኤው ይመርመር።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please think as human! It is not good to this extent of speaking strong words! God is the judge.

   Delete
  2. Asmermerew

   Delete
 12. ዘመድኩን እኔ እየሱስ ነኝ ቢለን እንኳን እናምነዋለን ታሁን ወዲህ ህርምሽን አውጪ ምድረ ግሪሳ ተንጫጩ ሀራጥቃ በርጣቃ ስድብ መማር የፈለገ የተዋህዶ ልጆች ጋ በያይነቱ አለ ኑና ተማሩ ።

  ReplyDelete
 13. የቤተክርስቲያንዋን ውሸትና ብዙ ነገሮችን ችሎ በተቀመጠ ነወው እንዴ የሚወገዝ???ወፍ አውጋዠ ሁሉ።

  ReplyDelete
 14. አሰግድ እንዲወገዝ መጀመራያ ጥያቄውን ያነሳው በላይ ወርቁ ነው በአዲስ አበባ አገረ ስብከት ስብሰባ ላይ

  ReplyDelete
 15. አሰግድ እኮ ከተወገዘ ቆየ፡፡
  አሁን ተረጋገጠ እንጂ

  ReplyDelete