Monday, May 22, 2017

ማቅ በኦሮሚያ ተማሪዎች ላይ በቋንቋቸው የሃይማኖት ትምህርትን እንዳይማሩ በማድረግ ያደረሰው በደል እንዲጣራ ሲኖዶሱ ወሰነ


 Read in PDF

መግለጫ በማውጣት የተጠናቀቀው የግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ በመግለጫው በመግለጫው የተነሣው ሌላው ነጥብ ማቅ በኦሮምያ የተለያዩ ዞኖች ከወለጋ፣ ከጅማ፣ ከአዳማ፣ ከድሬዳዋ፣ ከአምቦ ከሐሮማያና ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰባሰቡና ከዚህ ቀደም ለፓትርያርኩ ያቀረቡት አቤቱታ ታይቶ ውሳኔ ማግኘቱ ነው፡፡ በመግለጫው እንደ ተመለከተው በተማሪዎቹ ላይ ጠባቡና ትምክሕተኛው ማቅ የሃይማኖትን ትምህርት በቋንቋቸው እንዳይማሩ በማድረግ ያደረሰባቸውን በደል አስመልክቶ ጉዳዩ እንዲጣራ ተወስኗል፡፡
በአቤቱታው ላይ እንደተመለከተው ማቅ ተማሪዎቹን ወደግቢ ሲገቡ ከተቀበላቸው ጀምሮ “በአውደ ምህረቱ ላይ የሚተላለፈው የእግዚአብሔር ቃል መሆኑ ቀርቶ ነጋ ጠባ የአንድ ማህበር  የበላይነትና ልዕልና ትረካ፣ መቆምም ሆነ መስራት ያለብን ለቤተ ክርስቲያኗ ሳይሆን ለማህበሩ እንደ ሆነ፣ አጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ምንደኞች እንደሆኑና ብቸኛው የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ ማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ የሚተርክ የአንድ ቡድን” ትረካ መሆኑ እንዳሳዘናቸው በደብዳቤያቸው ገልጸዋል፡፡ ሌሎችንም ነጥቦች በመንሣት ማቅን መስመር እንዲያሲዙላቸው ጠይቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ የማቅ ብሎግ ሐራ ይህን የመግለጫውን የመጨረሻ ነጥብ ማቅን የሚነካ ሆኖ ስላገኘው ዘሎት፣ አብዝቶ ያበሳጨውንና በስፋት እንዲወራ የፈለገውን ነገር ግን ተቀባይነት ያላገኘውንና በመግለጫው ውስጥ ፈጽሞ ያልተነሳውን የዶ/ር አባ ኃ/ማርያም ለጵጵስና መታጨታቸውን ለማስተጓጎል የጎነጎነው ሴራ ላይ ጊዜውን አጥፍቷል፡፡ የኦሮሞ ተማሪዎችን ጥያቄ የያዘውንና ጥር 4/2009 ቀርቦ የነበረውን የተማሪዎቹን አቤቱታ ግን ምንም ሳይልበት አልፎታል፡፡
4 ገጽ ያለውን አቤቱታ እነሆ ይመልከቱ፡፡ 

ከዚህ ሌላ መግለጫው ያነሣው የመ/ር አሰግድ ሳህሉን መወገዝ ሲሆን ሲኖዶሱ ያወገዘበት መንገድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ ለመሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ ከአውጋዥ አስወጋዦቹም የተሰወረ አይደለም፡፡ አገልጋዩን ጠርቶ ማነጋገርና እውነት ሐሰቱን ማጣራት ሲገባ፣ ስሕተትም ከተገኘ የንስሐ እድል ሰጥቶ ለማቅናት ከመስራት ይልቅ ተንደርድሮ ውግዘት ውስጥ መግባት ከሲኖዶስ የማይጠበቅ አሳፋሪ ተግባር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በትክክለኛው ሂደት ውስጥ ሳይታለፍ የሚደረግ ውግዘት ተቀባይነት የሌለው ተራ ተግባር ይሆናል፡፡ ተቀባይነትም የለውም፡፡ በመ/ር አሰግድ ላይ ውገዘት መተላለፉ ከተሰማ ጀምሮ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ አውጋዥ አስወጋዡ ክፍል ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ መሰማቱና አለአግባብ ለተወገዘው ለአሰግድ ከፍተኛ ድጋፍ መቸሩ ወንጌልን በመስበክ የሚመጣውን ውግዘት የማያስተናግድ ትውልደ ወንጌል መነሳቱን አመልካች ነው፡፡
ወንጌል ሁል ጊዜ በተመቻቸ ሁኔታ ሊሰበክ እንደማይችልና ውግዘትና ስደት እንደሚታወጅበት የታወቀ ነው፡፡ ውግዘት እንዳይመጣ ካስፈለገ ዝም ማለት ወይም ወንጌልን ሳይሆን ሌላ ሌላውን መስበክ ነው መፍትሄው፡፡ በዚህ ጊዜ አሞጋሽ እንጂ አውጋዥ አይኖርም፡፡ መከበር እንጂ መወገዝ አይኖርም፡፡ ሰውን ነጻ የሚያወጣውን ወንጌል መስበክ ግን መናፍቅና ተሐድሶ ያሰኛል፡፡ ነገር ግን በዚህ በሰለጠነ ዘመን ተቀራርቦ መነጋገርና ለቤተ ክርስቲያን ችግር በጋራ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ውግዘትን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መውሰድ ዘመኑን ካለማየት የሚመጣና በዱሮ በሬ ለማረስ መሞከር ነው፡፡
ዘመኑ ለውግዘት ብዙ ቦታ የማይሰጥ መሆኑን ከግብጽ ኦርቶዶክስና ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የቅርብ ጊዜ ስምምነት አእምሮ ያለውና ዘመኑን የዋጀ ሁሉ መረዳት ይችላል፡፡ ራሱን ከጊዜው ጋር የማያራምድና የቀደሙ አንዳንድ ውግዘቶች እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ በሚል ፖለቲካዊ አጀንዳ እንጂ በጎላ ሃይማኖታዊ ልዩነት ላይ ያልተመሠረቱ መሆኑን ያልተረዳ ሃይማኖተኛ ነኝ ባይ ግን ለዛሬው የሃይማኖት ችግር ውግዘትን እንደ መፍትሄ ቢጠቀምበት ከኪሳራ በቀር ትርፍ የለውም፡፡  
በዚህ ዘመን ውግዘት ለዚያውም ተገቢውን ሥርዓት ያልተከተለ ውግዘት ቤተ ክርስቲያኗን ትልቅ ትዝብት ላይ የሚጥል፣ ይዞታዋም ከዕለት ወደ ዕለት እያሽቆለቆለ መምጣቱን በግልጽ የሚያሳይ፣ ሰውም እንደሌለባት የሚያስቆጥር ደረጃ ላይ መደረሱን የሚያጋልጥ፣ ቤተ ክርስቲያኗ ትርፍና ኪሳራዋን እንኳን መተመን የማትችልና ለግል ጥቅማቸው ባደሩና የወንጌል መሰበክ ሕዝቡን የሚያነቃና የእነርሱን ጥቅም የሚያስቀር መሆኑን በተገነዘቡ ክፉዎች የተቀነባበረ መሆኑን በግልጽ የሚያመለክት ነው፡፡
 

6 comments:

 1. Big shame on you! Koy gin enante mech new yemtafrut! Sew hulu endenante kalasebe sihtet new ende??? enkuanm aweknachihu! Leka Betraqoch nachihu:: Andit kntat timezuna lerasachihu Propaganda! Gin egnam awkenal gudguad misenal!!!

  ReplyDelete
 2. ሌላ ጊዜ ሥርዓትን ነቅፋችሁ ትጽፋላችሁ አሁን ደግሞ ሥርዓት ተፋልሷል ትላላችሁ አቋም ይኑራችሁ እንጂ! አውግዞ መለየት እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚቀጥል መሆኑን ማወቅ አለባችሁ ከዘመናዊነት ጋር የሚገናኝ አይደለም፡፡ አሰግድ እኮ የተወገዘው ኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም ሰው የሆነ ፍጹም አምላክ እንደሆነና ፈራጅ እንጂ አማላጅ እንዳልሆነ ከክርስቶስ ትንሳኤ ማግስት ጀምሮ ስታስተምር በኖረችው አሁንም እያስተማረች ባለችው የቀናችውን የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮን በመጻረር ክርስቶስን አማላጅ በማለት የኑፋቄ ትምሕርት እያስተማረና እያስፋፋ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ትምህርት ደግሞ በቀደሙት የቤተክርስቲያን አባቶች ዘንድም የተወገዘ ነበር፡፡ኑፋቄውን ደግሞ በሚያስተምር ሁሉ ላይ እሰከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ውግዘቱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
  ቀና ሃይማኖትን እና የሃገር ፍቅርን ለትውልዶች ስትሰብክ የኖረች፣ ጥበብና ሥነ ጽሑፍን በማስፋፋት ለዓለም የተረፈ ሃብት ያፈራችን ቤተክርስቲያን ለሆዳችሁ ስትሉ ከውጪ ኃይሎች ክፉ ምክር ጋር በማበር የታሪክ ተወቃሽ ባትሆኑ መልካም ነው፡፡

  ReplyDelete
 3. Now I know what exactly Mahibere kidusan is doing. When the people from Tigray published a bible in Tigrinya, Mahibere kidusan said it was from tehadiso. When afar Orthodox kids orthodox mezmur, Mahibere kidusan said it was from tehadiso. When Oromo people tried to teach their kids bible with afan Oromo, they said afan Oromo is from tehadiso. I see the trend. So if any Ethiopian doesn't teach or preach in Amharic, it is from Tehadiso. Other developed countries try to broadcast their religion through different languages, Mahibere kidusan try to dominate and influence other Ethiopian tribes through the Amhara language, Amharic. It is a disgrace.

  ReplyDelete
  Replies
  1. My brother this is not the reality, you only following this blog but go to gibigubae then ask for the oromos by what language they are learning, but for the whole it is difficult to teach in oromogna since the audience is from different setting with different language. The other thing what I want to say is for this blog before posting one word or phrase try to read and understand the bible then you will do otber things like preaching criticizing and comparing one with the other.
   Glory to Our Lord Jesus Christ and his Mother St. Mariam

   Delete
  2. My brother this is not the reality, you only following this blog but go to gibigubae then ask for the oromos by what language they are learning, but for the whole it is difficult to teach in oromogna since the audience is from different setting with different language. The other thing what I want to say is for this blog before posting one word or phrase try to read and understand the bible then you will do otber things like preaching criticizing and comparing one with the other.
   Glory to Our Lord Jesus Christ and his Mother St. Mariam

   Delete
  3. My brother this is not the reality, you only following this blog but go to gibigubae then ask for the oromos by what language they are learning, but for the whole it is difficult to teach in oromogna since the audience is from different setting with different language. The other thing what I want to say is for this blog before posting one word or phrase try to read and understand the bible then you will do otber things like preaching criticizing and comparing one with the other.
   Glory to Our Lord Jesus Christ and his Mother St. Mariam

   Delete