Tuesday, July 4, 2017

“እስመ አቡየ ወእምየ ገደፉኒ ወእግዚአብሔር ተወክፈኒ” (መዝ. 26፥10)ይህን መሪ ቃል መጥቀስ የተፈለገበት ምክንያት አለው፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት እየተባለ ቢጠራም እየተፈፀመበት ያለው ግፍ ሰሚና ተመልካች በማጣቱ፣ በችግሩ ሰለባዎች አንጻር ለቆመ ሰው ችግሩን ይህ መሪ ጥቅስ ሃይለ ቃል በመጠኑም ቢሆን ይገልፀዋል ተብሎ በመታሰቡ ነው፡፡ ይኸውም ንጉስ ዳዊት እንዳለውና የቤተክርስቲያን ሊቃውንት እንደሚተርኩት አንደምታ ዳዊት 26-27-1ዐ አባትና እናቴም ትተውኛል እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ ይላል፡፡
በአንድ አገር አንድ ንጉሥ ነበር ሕማመ ኮክሽ የሚባል ታመመ ይላል፡፡ በዚህ ንጉሥ ዙሪያ የነበሩ ጠንቋዮች አወቁ፣ መድሃኒት ፈልጉ ቢባሉ ከሰይጣን የሚገኘው መልስ ከድሮም ሰይጣን ነፍሰ ገዳይ ነውና (ዮሐ. 8፥44) ጠንቋዮች የሰጡት ወይም ያቀረቡት ሃሳብ ለእናት አባቱ አንድ የሆነ ልጅ አስመጥተህ እናቱ ይዛው አባቱ አርዶልህ በደሙ በፈርሱ ብትታጠብ ይሻልሃል ይሉታል። ንጉሥ የፈለገውን ማድረግ ይችላልና ንጉሥ ለእናት አባቱ ገንዘብ ከፍሎ በልጁ በምስኪኑ ደም ሊታጠብ አስመጣው። በእናቱ ያዥነት በአባቱ አራጅነት ተስማሙ፡፡ አባቱ ሊያርደው ሲል ዓይኖቹን ወደ ሰማይ ቀና እያደረገ አስቸገረ፡፡ ምን ታያለህ? አሉት ጥንቱን ለልማዱ ለልጅ የሚያዝኑ አባት እናት ነበሩ እነርሱ ጨክነው ሊያርዱኝ ተስማሙ፡፡ ጩኸት ሰምቶ የሚያድነውና የሚፈርደው ንጉሥ ቢጨክንብኝ ወዴት አቤት ልበል አለ ይላል፡፡

ይህ ታሪክና የነጎይትኦም ድርጊት የሚስማማ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም አለቃና ጸሀፊ ያለአግባብ አባረሩኝ፤ ያለ ምክንያት ተባረርኩ ተበደልኩ ብሎ አቤት ቢል፣ ተቸገርኩ ቢል፣ ፍትህ በመስጠት ፋንታ የተቸገረውን ሰው “እንዲፃፍልህ ከፈለክ ሃያ ሰላሳ ሺህ ብር አምጣ” ይባላል፡፡ ለዚያውም ደላሎቹ ቀና ከሆኑ ነው፡፡ ችግረኛው ተበድሮም ተለቅቶም በለስ ከቀናው ለጎይቶምና ለሠራዊቱ ጉቦ ከፍሎ ይመለሳል፡፡ ወደ ተመለሰበት ደብርም በአለቃው በፀሐፊው ፊት ንስሃ እንዲገባ ይደረጋል፤ ማለትም ሲሰርቁም ሆነ ጉቦ ሲቀበሉ ቢያይ ላይናገር ቃል ይገባል፡፡ እንኳን ለጉቦው የምንቀምሰው የለንም ያሉ ምስኪኖች አቤት ለማለት ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ ቢያመሩ፣ ፕሮቶኮሉነቱን ለግል ጥቅሙ በማዋል የሚታወቀው መ/ር ሙሴ ገ/ፃዲቅ ይከለክላቸዋል። የጎይቶኦምን እኩይ ሐሳብና አልጠግብባይነት እያወቀ ከጎይትኦም ጋር በመናበብ የጎይቶኦምን ክፋት አበጀህ ጐበዝ እያሉ ለሚገቡ ደግሞ ይፈቅድላቸዋል፡፡
ይህ ዘመን የኤሊን ዘመን ይመስላል፡፡ ኤሊ በእድሜው ሸምግሎ የእግዚአብሔር ሕዝብ በተመሠረተበት መንፈሳዊ እና ሥጋዊ ጎዳና በመምራት ያሳየው አንዳች መልካም እንቅስቃሴ ቢኖር ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረን ነበር፡፡ ይልቁንም በእርሱ የአመራር ድክመት ምክንያት ለእግዚአብሔር ሕዝብ መዋረድን እልቂትን አስከትሎአል፡፡ የኤሊ ጥፋት የእድሜ መጫን ብቻ ሳይሆን በወጣትነት ዘመኑ የሠራው መልካም ሥራ እና ጥበቃ አልተመዘገበም፡፡ ኃላፊነቱን እንደ ካህን ቤተሰብነቱ እንኳን መምራት ያልቻለ ሰው ነበር፡፡ መልካም ካህን መሆን የሚገባው ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው ማለት ነው (1ጢሞ. 3፥4)፡፡ ዛሬም እንደ ኤሊ የእግዚአብሔርን ቤት እና የሕዝቡን አስተዳደር ኃላፊነት ተቀብለውና ቃል ገብተው በጥቅማጥቅም ላይ ብቻ የሥጋ እና የመንፈስ ዓይኖቻቸውን ያሳረፉ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክቡር ስም መሰደብ ለአስተምህሮ መበከል ለሥርዓተ ቀኖና መጕደል ደንት ቢስ የሆኑ የዘመናችን ኤሊዎች አሉ፡፡ ምእመናኑን የሚፈልጉአቸው እነርሱ እንደ ጥጃ ምእመናኑ እንደ ጥገት ሆነውላቸው ጠብተው የማይጠግቡትን ወተት ለመምጠጥ (ሕዝ. 34፥1-31 ማቴ. 23፥14) ብቻ እንጂ ምእመናኑ ስለሚደርስባቸው የሞራል ዝቅጠት ከቶ አይገዳቸውም፡፡ የእግዚአብሔር ሕግ እንዲመራቸውና እንዲገስጻቸው አይፈልጉም በጥቅም ፈዝዋል ደንዝዘዋል፡፡
የኤሊ ዓይኖች በጥቅም እንደፈዘዙ
ኤሊ ጆሮቹ ማድመጥ የሚችሉት አበል ተቀነሰ፣ ጥቅማጥቅም ተጓደለ፣ የዘንድሮ አስራት በኩራት ገቢ ከአምናው አነሰ፣ የዘንድሮዎቹ የመስዋት እንስሳት አልሰቡም የሚሉትን ድምጾች ነበር፡፡ እንደዚህ ባለ ሁኔታ የፈዘዙት የዔሊ ዓይኖች የእግዚአብሔርን ቃል ያነቡ ዘንድ ብቁ አይደሉም፡፡ ራእይ ቢመጣ ማን ያስተውላል? መልእክት ቢመጣ ማን ይሰማል? (1ሳሙ. 2፥12)፡፡
ዔሊና ልጆቹ ምናምንቴ ሆነዋል
 እርሱ ያልሆነውን የሚሆኑ ልጆች ይወልድ ዘንድ መቼም አይጠበቅም (ኢዮ. 14፥4)፡፡ ምናምንቴዎቹ የኤሊ ልጆች የሚያሳስባቸውን የመስዋእቱን ስብ ይሠርቃሉ (1ሳሙ. 2፥13)፡፡ ከሕብስቱ መስዋእት ላይ መስዋእት አቅራቢዎቹ ሊቀበሉ የሚገባውን ቡራኬ ይነጥቃሉ፡፡ (ዘሌ.7፥11-14)፡፡ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት ራሳቸውን የሰጡትን ደናግሉንና ባልቴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ (1ሳሙ. 2፥22)፡፡
አስራቱንና በኩራቱን ወደ ግል ኪስ ይጨምራሉ፡፡ የሊቀ ካህናት ልጆች መሆናቸውን መከታ በማድረግ ለአምልኮተ እግዚአብሔር የወጡትን ምእመናን ያዋክባሉ ንጹሐን የሆኑ አገልጋዮችን ያሳድዳሉ፡፡ በዚህ ምክንያት የኤል ልጆች ምናምንቴ ተባሉ፡፡
ልክ እንደ እነ ጎይቶም የማፍያ ቡድን ሀልዎተ እግዚአብሔርን የማያምኑና ንፁሐን ታማኝ የሆኑ አገልጋዮችን “ያልገባው ፋራ” እያሉ ያሳድዳሉ፡፡ ከሙዳየ ምፅዋት ሰርቆ የመጣውን ያሳድጋሉ፣ ያበረታታሉ ምሁሩን መሐይም መሐይሙን ሊቅ እያሉ ይሾማሉ፡፡ ምስኪኑን እና ታማኙን ገፍትረው ሌባውን ብልህ ብለው ይሾማሉ፡፡ ጎይቶም በክፋቱ እንዲቀጥል ካልተሰለፉለት ይበቀላሉ፡፡ ከመቀሌ እስከ ወሎ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይፈጽማሉ፡፡ በተለይ በስመ ወሎ የፈጸሙት ታሪካዊ ወንጀል ይቅር ሊባል የማይችል ነው፡፡ የተራ ሰራተኛውንና ያለቆቹን እንተወውና በሊቀ ስዩማን ተስፉ እና በሊቀ ስዩማን ፊለቀ ጩኒ ካለምንም ጥፋት ጊዜ የሰጠው የነ ጎይቶም ፋሽስታዊ አስተዳደር ያለ ተጠያቂነት ወሎ በምስራቅ ይሁን በምእራብ የማያውቁትን ልጆች የትውልድ ሐረግ ቆጥሮ በግፍ ከቤተክርስቲያን እንዲሰደዱ አደረጉ፡፡ ሰበካ ጉባኤው የፈቀደውን ጉቦ ያስከፍላሉ፡፡ ፐርሰንት ከፍሎ ግዴታውን ተወጥቶ እያለ አንተ ራያ ነህ እገሌ መቀሌ ነው ትግሪኛ ተናጋሪ ወሎዬዎች ናቸው በማለት በጎጠኛ አስተሳሰብ ሕዝብን ከሕዝብ ይከፋፍላሉ፡፡ በደሃው ጥቃት ውስኪ እየተራጩ ይዝናናሉ፡፡ የእገሌ ደብር ፀሐፊ ሒሳብ ሹም ቁጥጥር አለቃ ስንት ያወጣል እያሉ ውስኪ ቤት ሽያጭ ይፈጽማሉ፡፡ ይህ ሁሉ አሉባልታ እንዳልሆነ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር የሆነው ናሁ ሰናይ ወሎዬ ስለሆነ ስራ ሲሰራ እስካሁን ድረስ በታሪክ ፈጽሞ ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ እና ፓራፍ ማድረግ የአስተዳደሩ ሥልጣን እና ተግባር ሆኖ እያለ ፓራፍ እንዳያደርግ አግተው በመያዝ የማይመለከተውን ሰው የሐቀኝነት ተምሳሌ ይባል የነበረውን ቀሲስ ኃይሉን የአሁኑን የጎይቶም ተላላኪ በመሆን በማይመለከተው ሥራ እየሠራ ፓራፍ አድራጊ በመሆን ትልቅ ስህተት እየሠራ ይገኛል፡፡
ለዓመፀኛይቱና ለረከሰች ለአስጨናቂይቱም ከተማ ወዮላት! ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፤ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም። በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚያገሡ አንበሶች ናቸው፤ ፈራጆችዋም እስከ ነገ ድረስ ምንም እንደማያስቀሩ እንደ ማታ ተኵላዎች ናቸው። ነቢያቶችዋ ቅሌታሞችና ተንኰለኞች ሰዎች ናቸው፤ ካህናቶችዋም መቅደሱን አርክሰዋል፥ በሕግም ላይ ግፍ ሠርተዋል። እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፤ ክፋትን አያደርግም፤ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም። አሕዛብን አጥፍቻለሁ፤ ግንቦቻቸው ሁሉ ፈርሰዋል፤ መንገዳቸውን ማንም እንዳያልፍባት ምድረ በዳ አድርጌአለሁ፥ ከተሞቻቸውም ማንም እንዳይኖርባቸው፥ አንድስ እንኳ እንዳይቀመጥባቸው ፈርሰዋል።” (ሶፎ 3፥1-6)፡፡
ይህ ዘመን እና የኤሊ ዘመን የሚያመሳስለው
አንዲት መንፈሳዊ ድርጅት አንዲት ቤተ ክርስቲያን በምናምንቴ አገልጋዮች ስትሞላ ምናምንቴ ልጆችን ያፈራ አባት ሊቀ ካህናት ሆኖ ሲመራት ከማየት ጋር የሚተካከል ሌላ ምን ክፉ ነገር ይኖራል? ሊቀ ካህናቱ ዓሊ ልጆቹ የሚሠሩትን ክፉ ነገር አሳምሮ ያውቅ ነበር ስለ ክፉ ስራችሁ ከዚህ ሕዝብ ሁሉ ሰምቼአለሁ ብሎአልና፡፡ 1ሳሙ. 2፥23-24 ላይ እያደረጉ ያለውን ከአንድ ሰው ወይም ከሁለት ሰዎች ሰማሁ አላለም ከዚህ ሕዝብ ሁሉ ሰምቻለሁ አለ፡፡
ዛሬም የእግዚአብሔርን ቤት አደራ ሕዝቡን በማስተዳደር ኃላፊነት የተቀበሉ ሆነው እያለ በቤተ ክርስቲያን የሰገሰጉአቸው ምናምንቴ ልጆቻቸው ሰርቀው ዘርፈው በሚያመጡላቸው ሃብትና ንብረት አብረው ተጠቃሚዎች የሆኑ ስለ ምናምንቴ ልጆቻቸው አድራጎት የሚሰሙትን እንዳልሰማ፣ የሚያዩትን እንዳላየ ሆነው በምናምንቴ ልጆቻቸው ታጥረው መኖርን የመረጡትን እና የሚመርጡትን የዘመናችንን ልጆች እንኳን እግዚአብሔር ምእመናኑም ቢሆኑ በሚገባ ያውቋቸዋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርና ምእመናኑ ቢናገሩም ኤሊዎች አይሰሙም፡፡ ለእንስሳይቱ ኤሊ እንደ ልብስ የተሰጣት የድንጋይ ልብስ ለቤተ ክርስቲያን ኤሊዎች የልባቸው መሸፈኛ ሆኗል ቢባል በእውነት ያስኬዳል፡፡
የካህኑ የኤሊ ልብ መደንደን
ክብር ከእስራኤል ለቀቀ
በዚያ ዘመን እስራኤል ከዘወትር ጠላቶቻቸው ከፍልስጤማውያን ጋር ሊዋጉ እንደ ወጡ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል (1ሳሙ. 4፥22)፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ምንጊዜም አሸናፊነቱ የታወቀ ሆነና ውጊያው ቶሎ ተጀመረ፣ በፈዛዛው ደንጋዛው ኤሊና በልጆቹ አመራር ስር ያሉት እስራኤል መሳሳታቸውን አላስተዋሉም፡፡ አሸናፊነታቸው ከእግዚአብሔር ሃይል የተነሳ እንደነበር ከእነርሱ ጀግንነት ከጠላቶቻቸው ፊሪ መሆን እንዳልነበር ዘነጉ፡፡ እንደ ወትሮው አይዋጋላቸውም ንቀውታል አሳዝነውታል፡፡ ሥርዓቱን አጕድለዋል ክብሩንም ተዳፍረዋል፡፡ ለምን ብሎ ከዚያ ሕዝብ ጋር ይወጣል? ለምንስ መከታ ይሆናል? ምክንያቱም ያከበሩኝን አከብራለሁ፣ የናቁኝም ይናቃሉ ብሎአልና (1ሳሙ. 2፥30)፡፡ ከእነዚህ ምናምንቴ ልጆች  ኃጢአትና በደል የተነሣ በታሪካቸው እስራኤላውያን ገጥሞአቸው የማያውቅ ኪሣራና እልቂት ደረሰ፡፡ በአንድ ጀምበር ብቻ ኤሊና ልጆቹን ጨምሮ ሰላሳ ሺህ ሰው አለቀ፡፡ ታቦተ ጽዮንም ተማረከች (1ሳሙ. 4፥10-11)፡፡ አስደንጋጩ ዜና ክብር ከእስራኤል ለቀቀ፡፡ እግዚአብሔር ከእስራኤል ተለየ፡፡ በወቅቱ በሰዓቱ የተወለደ ልጅ ኢካቦድ ተባለ (1ሳሙ. 4፥17) ኤሊና ምናምንቴ የተባሉ ልጆቹ እና የዘመናችን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ይመሳሰላሉ፡፡
የኤሊ ቤት ኃጢአት አይሰረይም   
እነሆ በኤሊ እና በቤተ ሰቡ ላይ የተገርሁትን እፈጽማለሁ አለ እግዚአብሔር ስለዚህ የኤሊ በደል በመስዋእት አይሰረይም (1ሳሙ. 3፥1-4፤ 1ሳሙ. 2፥25)፡፡ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ቢበድል እግዚአብሐር ጣልቃ ገብቶ ይፈርዳል፣ ነገር ግን ሰው እግዚአብሔርን ቢበድል ማን ይማልድለታል (1ሳሙ. 2፥25)፣
የዘመናችን ኤሊዎች ምን ይጠብቃቸው ይሆን?
የነጎይቶም ቡድን ከኤሊ ምናምንቴ ልጆች በእጥፉ የበለጠ ስላጠፋ ስለ ረከሰ ግፍ ስለ ሰራ ቅጣታቸው እጥፍ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱም የሞት አገልግሎት የነበረው ይሄን ያህል ካስቀጣ ይልቁንም የአዲስ ኪዳን ስርአትና ህግ በክርስቶስ የተዋጀችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ምን ያህል ይከፋ ይሆን? “የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?” (ዕብ. 10፥29)፡፡
አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።” (ዕብ. 6፥4-7)፡፡
“የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥” (ዕብ. 10፥26)፡፡
ይህን የእግዚአብሔር ቃል የጠቀስኩት ጎይትኦምና ቡድኑ የማያውቁት ሆነው ሳይሆን ገንዘብ ሐሺሽ ሆኖ ስላደነዘዛቸው የማንቂያ ደወል ቢሆናቸውና ጠፍተው እንዳይቀሩ ንስሐ ቢገቡ ለማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ሸጠው አሳደው አልበቃ ብሏቸው እንደ ጣሊያን ማፍያ ጡንቻቸውን ስላፈረጠሙና የሚጠይቃቸውም ህግ ስለሌለ የገዳማቱን ቅርስና ወርቅ በጎይትኦም ሽፋን ሰጪነት እንዳይዘርፉት በከተማው ውዥንብር ስላለ ነው፡፡
ከሁሉ የሚያሳዝነው የሌሎቹን እንተወውና አራቱ መነኮሳት እየፈጠሩት ያለው ውዥንብር አሳሳቢ ሆኗል፡፡ እነዚህ መነኮሳት፦ 1ኛ. አባ ጥዑመ ልሳን የልደታ አስተዳዳሪ
                   2ኛ. አባ ፍቅረ ማርያም የምስካየ ሕዙናን መድኃኔዓለም አስተዳዳሪ
                   3ኛ. አባ ኃይለ መለኮት የተክለ ሃይማኖት አስተዳዳሪ
                   4ኛ. አባ ገ/ሥላሴ የቅድስት ሥላሴ አስተዳዳሪ ጎይትኦም በሚሰራው ክፋት የሚዝናኑና ይበል አበጀህ ወሎን አጠፋህልን ራያን አደቀከው እያሉ የሰዎች መሰደድ የሚያዝናናቸው እውነቱን ውሸት ውሸቱን እውነት እያሉ ቅዱስ ፓትርያርኩን በውሸት እየመሰከሩ የሚያሳስቱ ናቸው፡፡ በእግዚአብሔር ፊት የሚናገሩት ከንቱ ነገር ዋጋ የማያስከፍል መስሎአቸው ይሆናል፡፡ “እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤” ማቴ. 12፥36፡፡
“እነዚህ ውሃ የሌለባቸው ምንጮች” የተባሉ 2 ጴጥ. 2፡17 “እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፥ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው፥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ። የሰላምን መንገድ አያውቁም፥ በአካሄዳቸውም ፍርድ የለም፤ መንገዳቸውን አጣምመዋል፥ የሚሄድባትም ሁሉ ሰላምን አያውቅም።” ኢሳ. 59፡7-9 የተባለላቸው ይመስል፣ አራዳ ጊዮርጊስን፣ ቦሌ መድኃኔዓለምንና ሲኤምሲ ሚካኤልን ለማግኘት የማይቆፍሩት ጉድጓድ የማይዋሹት ውሸት የለም፡፡ የራሳቸውን ልማት በማልማት ፋንታ ሰዎች ያለሙላቸውንና የሰበሰቡላቸውን ገንዘብ ለመዝረፍ አንዳቸው መኪና እንሸልምሃለን፣ አንዳቸው እየዋሸን ለክፋትህና ለድንቁርናህ ሽፋን እንሰጥሃለን በማለት ጠዋት ማታ እየተጫረቱ ይገኛሉ፡፡ ወደ ፓትርያርኩ በመግባት የውሸት ምስክርነት እየሰጡ ከቅ/ፓትርያርኩ ዘንድ ከወጡ በኋላ ፓትርያርኩ ላይ በመሳለቅ ጥሩ ነገር ይናገራሉ ብለን ስንጠብቅ “የጎይትኦም ትልቁ ችሎታና የሥራ ዕውቀት ስደውልለት ስልኬን ቶሎ ብድግ ነው የሚያደርገው” እያሉ ስልክ ማንሳትን እንደ ትልቅ ችሎታ እንዴት ይቆጥሩታል? እያሉ ይሳለቁባቸዋል፡፡ በእርግጥም የፓትርያርኩ መገምገሚያ ስልክ ማንሳት ከሆነ ያሳፍራል፡፡ ጎይትኦምስ ከዚህ የተለየ ምን አደረገ? ሰርቀውና ቅርስ ዘርፈው ኪሱን የሚሞሉለትን ጎበዝ ባለ ችሎታ እያለ አማካሪ ያደርጋቸዋል፡፡ በዕውቀታቸውና በታማኝነታቸው እውነት የሚሰሩትን ግን ያሳድዳቸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከአራቱ መነኮሳት የአባ ጥኡመ ልሳን ምስክርነት የሚለየው ካላቸው የቤ/ን ዕውቀትና የአገልግሎት ዘመን ሲታይ ለቤ/ኒቱ በሞያቸው ብዙ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ ለጵጵስናም ማንም አይቀድማቸውም፣ አሉ ከሚባሉ መነኮሳት አንዱ ናቸው ተብሎ ግምት ከተሰጣቸው አባቶች አንዱ ነበሩ፡፡ ታዲያ ለምን ቀሩ? ቢባል ምርጫው የመንፈስ ቅዱስ ቢሆንም ብዙ ሰዎች የሚጋሩት ግን የአቡነ እንድርያስ ተቃውሞ ሳይሆን የአፅባዕተ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ጣት) ፍርድ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ምክንያቱም አባ ጥዑመ ልሳን ጎይትኦም ክፋትና ብልሹ ስነምግባር ያለው መሆኑን ማንም ሳያስረዳቸው እሳቸው በሚያስተዳድሩት ቤተክርስቲያን የሰራውን ሙስናና በደል፣ ሠራተኞች በስራ ገበታቸው እያሉ እንደሌሉ አድርጎ አየር በአየር ሲያስቀር ደመወዝ ያለ ጉቦ አላጸድቅም ብሎ ሁለት መቶ ሺህ ብር ጉቦ ወጪ ሲደረግ በኋላም ፓትርያርኩ ስለሰሙ እንዲመለስ በመባሉ ቼኩ ለመታጠፉ ህያው ምስክር ናቸው፡፡
እንዲህ ዓይነት ሙሰኛ መሆኑን እያወቁ ግን ፓትርያኩ ዘንድ ገብተው “እውነተኛ ነው” ብለው በመመስከር ይቀጥል ብለው ጥፋቱን በመሸፈን ከአመፀኛ ጋር መሰለፋቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ቴቄል ማለት በሚዛን ተመዝነህ ቀለህ ተገኘህ የተባለ ከላይ ከእግዚአብሔር የመጣ ፍርድ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ከእሳቸውም ሞያና አስዋጽኦ አንጻር አንዳንዶቹ ተማሪዎቻቸው ሊሆኑ እንኳን የማይገባቸው ሰዎች ናቸው የተሾሙት፡፡ እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር አባ ጥዑመ ልሳን ከሚጠበቅባቸውና ከነበራቸው ስም ለማለት ነው እንጂ በክፋትና በዘረኝነት እነ አባ መለኮትና አባ ገ/ሥላሴ ይከፋሉ ለማለት አይደለም፡፡
እነዚህ መነኮሳትና አንዳንድ ኃጢአት በቃን የማይሉ ፀሐፊዎች ቤተክርስቲያኒቱን እንደ ጠላት ቤት በመበዝበዝ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጎይቶኦም የአቅም ማነስ ችግር ስላለበት በባሕሪውም ጭንቁር ስለሆነ አያስተውልም፡፡ ከጎተራ እስከ ሲኤምሲ በእህቶቹና በቤተሰቦቹ ስም ኮንዲምኒየም እየገዛ አዲስ አበባ እንኳን ከገባ ሁለት ዓመት ያልሞላው ሆኖ እያለ ያለ ጠያቂ በአቋራጭ ይህን ሁሉ ሃብት ሲያካብት፣ ሌሎች ምስኪኖች ከ20-30 ዓመት ርስታችን ብለው አገልግለው ያቁዩአትን ቤተ ክርስቲያን ድሆችን እያሳደደ እነሱን ሸጦ ሃብት ያካብታል፡፡ ለእሱ ድጋፍ የሰጡትን እየለየ በየ3ወሩ አለቆችን ሳይቀር ከደብር ደብር ይቀያይራል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ እንዴት እምነት አልባ ለሆነ ሰው፣ በሞያ ደረጃም ተንስኡ እና ፀልዩ ለማይልና ለማይቀድስ ሰው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ሊቃውንት ይመራል ብለው አሳልፈው ሰጡት? ይህስ የቤተክርስቲያንን ክብር ይነካል፣ ሌላው የጎይቶም ወሬ ነበር እራሱን ለማዳን ነው ተብሎ ይገመት የነበረው ወሎዬዎቹን አጥፋ ብለውኛል ፓትርያርኩ ምክንያቱም የአቡነ ሕዝቅኤል አገር ሰዎች ናቸው ከእሳቸው የመጣ ትእዛዝ ነው ብሎ ያስወራል፡፡ የእሳቸው እጅ እንዳለበት የሰሞኑ በክፍለ ከተማ ይሰሩ የነበሩ የወሎ ተወላጆች የዘር ማጥፋት ዘመቻ በጎይቶም ብቻ የተፈፀመ አይመስልም፡፡ ሲቀጥል ፓትርያርኩ የሰጡትን የኃላፊትነት ለፖለቲካ ፍጆታ እያዋለው ነው፡፡ ኮሎኔል እገሌ አጎትዋ ነው፣ እገሌ ደህንነት ዘመዱ ነው እያለ ለማስፈራሪያ በመጠቀም የቤተክርስቲያንን ውድቀት እያፋጠነ ይገኛል፡፡ እውነት የመንግሥት አካላት ጎይቶም የሚጠቅሳቸው ግለሰቦች እንዲህ ዓይነት አሳፋሪ ድርጊት ይደግፋሉ? ይህን በሂደት እናየዋለን፡፡
መ/ር ጎይቶም ከከሳቴ ብርሃን መቀሌ ጀምሮ ክፋትና የሙስና የተለማመደ እንደሆነ አንድ ምሳሌ በመጥቀስ የሚናገሩ አሉ፡፡ ያላገኘውን ግሬድ ግደይ በየነ የተባለ የሬጅስትራር ሠራተኛን አታልሎ በኮሌጁ መ/ር ሠራተኛ ተብሎ ለመቅረት B የነበሩ ሦስት ትምህርቶችን ወደ A እንዳስቀየረና የሬጅስትራር ሠራተኛ የነበረ ግለሰብም በጎይቶኦም ምክንያት በከባድ ማስጠንቀቂጠያ እንደ ታለፈ ሁሉም የሚያውቀው ሐቅ ነው፡፡ የመ/ር ጎይቶም አጭበርባሪ ባሕሪ መታየት የጀመረው በዚያ ጊዜ ነው፡፡ ይህን መጥቀስ ያስፈለገው የጎይቶም ባህርይ አንዳንድ ሰዎች አሁን እየሠራው ያለውን መሰሪነት ሰዎች አሳስተውት ነው እንጂ የእሱ ባሕሪ አልነበረም የሚሉ አንዳንድ ሰዎች ስላሉ ነው፡፡ አብረው የኖሩና የሚያውቁት የተማሩ ግን በፍጹም አንዳንድ የክፋት ቅመም  ጨምሮበታል እንጂ ሲጀመር በክፋት የተሞላ ፍጥረት ነው ብለው ያስረግጣሉ፡፡ እውነትም የጎይቶም ክፋት ሁለገብ ነው ለምሳሌ፡-
1.     ጎጠኝነት
2.    አስመሳይነት/መሰሪነት
3.    ሙሰኝነት/ዘራፊነት
4.    ውሸት
5.    ጨካኝነት
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ባሕርያት በሌሎች ስራ አስኪያጆች በመጠኑም ቢሆን የተገለጹና የተለመዱ ነበሩ፡፡ እርሱ ግን ወደ አምስቱ ሕዋሳት ከፍ አድርጓቸዋል፡፡ እስኪ እንመልከት በዚህ ዘመን በሀገሪቱ የተስፋፋውን የዘረኝነት አስተሳሰብ እንዲስተካከል ብዙ ቅን አሳቢዎች በልዩ ልዩ መንገድ መከባበርንና መቀባበልን እንዲሁም የሰውን እኩልነት እየሰበኩ ባለበት ሁኔታ ጎይቶም እንዴት አንድን አገር በሙሉ ጠላት ያደርጋል? በአቡነ ሕዝቅኤል ምክንያት የወሎ ተወላጆችን በሙሉ ጠላት አድርጐ በመፈረጅ ጉዳዩን ጂኦግራፊያዊ በማድረግ ከራያ እስከ መቀሌ ድረስ ትግሪኛ ተናጋሪ ወሎየዎች ናቸው ብሎ በአቋም ማመልከቻ አላይም አልቀጥርም በማለት አንድም ሰው ሳይቀጥር ትልቅ የሆነ የታሪክ ጠባሳ አስቀምጦአል፡፡ ዘረኝነትን አጥብቃ መቃወም ካለባትና ሰው ሁሉ እኩል መሆኑን መስበክ ከሚጠበቅባት ቤተ ክርስቲያን ስራ አስኪያጅ እንዲህ ዓይነቱ ዘረኛ አመለካከት መታየቱ ያሳዝናል፡፡
ከቀሲስ ማንአህሎት

No comments:

Post a Comment