Friday, July 7, 2017

የተሳሳተው ማን ነው? ብፁዕ አቡነ በርናባስ ወይስ የማህበረ ቅዱሳን ጆቢራዎች?በቅርቡ ታላቁ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርናባስ በአሜሪካ በታላቁ ካቴድራል በድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ በዕለተ ሰንበት የወንጌል ትምህርት በሚያስተምሩበት ሰዓት ብዙ ሊቃውንትና ካህናት እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት እጅግ ደስ በሚልና ልብን በሚማርክ አቀራረብ ነገረ ድኅነትን /soteriology/ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገውና ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮውን ጠንቅቀው ለሕዝበ ክርስቲያን በሚገባ መልኩ ያስተማሩ ሲሆን ከትምህርቱም በኋላ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና ካህናት እንዲሁም በወቅቱ ትምህርቱን እስከ መጨረሻው በደንብ ሲከታተሉ የነበሩ ምእመናን ለብፁዕነታቸው ያላቸውን አክብሮትና በሰጡትም ትምህርት የተሰማቸውን ደስታ በሚገባ ሲገልጹ ነበር።


እኛም በዕለቱ በቦታው ላይ ስለነበርን ትምህርቱን በሚገባ  ስለ ተከታተልን እንዲህ ዓይነት ለወንጌል የጨከኑ እውነትን ሳይሸቃቅጡ ገልጸው የሚያስተምሩ አባት እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያናችን ስለ ሰጠን ከልባችን አመስግነናል ።
አለመታደል ሆኖ ግን አባቶችን መስደብና ማዋረድ የቤተክርስቲያንንም ክብር በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በማራከስ ለአሕዛብና ለተለያዩ ቤተ እምነቶች ቅድስት ቤተክርስቲያንን መሳቂያ መሳለቂያ እያደረጋት የሚገኘው «ማህበረ ቅዱሳን» እያለ እራሱን የሚጠራው የአጋንንት ማህበር የእኚህን ታላቅ አባት ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በማብጠልጠልና በመሳደብ ትውልዱ በአባቶች ላይ ክፉ ቃል እንዲናገርና አባቶችንም እንዲያዋርድ የስድብ ቃል ሲያለማምዱ ሰንብተዋል።

አባይነ ካሴ፣ ዘመድኩን በቀለ እና ንዋይ ካሳሁን የሚባሉት የማህበረ ቅዱሳን ተላላኪ ጆቢራዎች ያለ አቅማቸውና ያለ እውቀታቸው የሊቀ ጳጳሱን ትምህርት ሲሰድቡና ሲያሰድቡም ሰንብተዋል። እነዚህ ሰዎች ብዙ ጊዜ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለሃይማኖት ቀናኢ በመምሰልና ለኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ራሳቸውን እንደ ብቸኛ ተቆርቋሪ በማስቀመጥ እንኳን ሊናገሩት ቀርቶ ሊሰሙት የሚከብድ ተራ የወረደ ቃላት በመጠቀም የቤተክርስቲያን አባቶችን ሲሰድቡና ሲያዋርዱ የሚውሉ ከእነርሱም አልፎ ተርፎ ትውልዱ ለአባቶች ክብር የሌለው፣ አመጸኛ፣ ተሳዳቢ፣ ትዕቢተኛ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ከልቡ የራቀው እንዲሆን እያስተማሩና እያለማመዱት የሚገኙ ክፉ የዲያብሎስ መልእክተኞች ናቸው።

ምንም እንኳ እነዚህ ልባቸው በትዕቢትና በክፋት የተሞሉ ደንዳኖች ለጊዜው ራሳቸውን እንደ አዋቂ በመቁጠር በአረጋውያን አባቶች ላይ ስድብና ዘለፋን ቢያበዙም ጊዜው ሲደርስ ከእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ከቶውንም ሊያመልጡ አይችሉም በተለይ ዘምድኩን በቀለ የአሁኑ አቡነ በርናባስ የቀድሞው አባ ወልደ ትንሳኤ አያልነህ በርካታ ስብከቶቻቸውን በነጻ ፈቅደውለት አባዝቶ እየሸጠ ይጠቀምና ገንዘብ ይሰበስብ የነበረ እንዲሁም ተቸገርኩኝ ብሎ በእግዚአብሔር ስም ሲማጸናቸው ምእመናንን አስተባብረው ገንዘብ እየላኩ ይረዱት የነበሩ ሲሆን ስለ ቅዱሳት መካናት ከሰዎች የገለበጠውን መጽሐፍ ማሳተሚያ አጣው ሲላቸው ሙሉ የእትመት ወጪውን ሸፍነው አሳትመውለት እንደ ነበር እኛም እርሱም እግዚአብሔርም የምናውቀው ሐቅ ነው። በዚህ መጽሐፍም ላይ ታላቁ ሐዋርያ እያለ ያሞካሻቸው እንደነበር በግልጽ የምናየው የቅርብ ጊዜ መረጃ ነው፤ ሌሎችም እጃችን የገቡና ጽፎ ሲልካቸው የነበሩ ደብዳቤዎች የአባ ወልደ ትንሣኤን ታላቅ የወንጌል አገልጋይነት የሚመሰክሩ እውነተኛ የቤተክርስቲያን አባትነታቸውን የሚያረጋግጡ ነበሩ፤ እንደ ይሁዳ ልቡ ውስጥ ሰይጣን የነገሠበት ይህ ክፉ ልብ ያለው ወጨት ሰባሪ ዛሬ ግን የዚህ የአጋንንት ማኅበር ጭሎ ተላላኪ ሆኖ በሐሰት ስማቸውን በአደባባይ ሲሰድብና ሲያሰድባቸው ይገኛል እግዚአብሔር ግን በልጆቹ ይቀጣዋል።እነዚህ  የጥፋት ልጆች አባይነህና ዘመድኩን  በቤተክርስቲያኒቱ ትምህርት ያላለፉ ከአባቶች እግር ሥር ቁጭ ብለው ዳዊት ያልደገሙ፣ ውዳሴ ማርያም ያልቆጠሩ፣ ጸዋትወ ዜማ በዞረበት ያልዞሩ፣ ሰዓታትና ቅዳሴ ፈጽሞ ያልተማሩ፣ ብሉያትና ሐዲሳትን ከየትኛውም ተቋም ተምረው ያልተመረቁ፤ በሃምሳ አመታቸው ራሳቸውን ዲያቆን እያሉ የሚጠሩ ማፈሪያዎች በጆሮ ጠገብ ከዚህም ከዚያም የቃረሟትን ጥራዝ ነጠቅ ጩኸት እንደ እውቀት ቆጥረው ትውልዱን በድንቁርና ጨለማ እንዲኖር ሊቃውንትና መምህራንን ሲያሰድቡ የሚኖሩ እቡያን ናቸው። አብይነህ ካሴና ዘመድኩን በቀለ ሁለቱም እስከዛሬ ለሕዝብ ያልተገለጠ የወረደ ስብእና ያላቸው ሲሆን በተለይ አባይነህ ካሴ ከቤት ሰራተኛው ጋር በዝሙት ሲረክስ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ከሚስቱ ጋር በተደረገው ከፍተኛ ጸብ ጉዳያቸው እስከ ፍርድ ቤት ደረጃ ደርሶ መዝገብ የተከፈተበት በኋላ ግን የማህበረ ቅዱሳን ሰዎች ጉድ ሆነናል ይሄ ከባድ ቅሌት በሕዝብ ከተሰማ ገበናችን አደባባይ መውጣቱ ነው ብለው በብዙ ጭንቅና ልመና ከሚስቱ ጋር አስማምተው እንዲቀመጥ ቢያደርጉትም ይህ ክፉ መንፈስ የተጸናወተው የዲያብሎስ ማደሪያ ግን አሁንም አርፎ አልተቀመጠም።


እነዚህ የረከሰ የግል ስብእና ያላቸው አስመሳዮች እንኳን ሕዝብን ለማስተማርና ብፁዐን አባቶችን ለመስደብ ቀርቶ ቤተክርስቲያን አውደ ምኅረት የማያስቆም ርኩሰት የሞላባቸው ጋጠወጥ ግለሰቦች ናቸው ይህንን ወደፊት በስፋት ይዘን እንመጣለን።
በቲያንስ ንግድ የብዙ ሰዎችን ገንዘብ አጭበርብሮ በልቶና ብዙ የአረብ ሀገር ሴት እህቶቻችንን ደም እንባ አስለቅሶ መንግስት በወንጀል ሲፈልገው በሃይማኖት ምክንያት ተሰደድኩኝ እያለ ዛሬም ሕዝብን የሚያጭበረብረው ዘመድኩን በቀለም ብዙ ጉድ ያለበት ሰው ነው።

ዘመድኩን በቀለ በአረብ ሃገር ኑሯቸውን ለማሸነፍ ደፋ ቀና ብለውና ወገባቸው እስኪበጠስ ድረስ ለፍተው ለዓመታት ያጠራቀሙትን የምስኪን እህቶቻችንን ገንዘብ በሃይማኖት መምህርነት ስም አጭበርብሮ የጠፋ ጨካኝና አረመኔ ሰው ነው። አረብ ሀገር ያሉ እህቶች የዋሕና ቅን መሆናቸውን አይቶ ከዘማሪ ልዑል ሰገድ ጋር የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ስም እየጠሩና በስሟ እያታለሉ እህቶቻችን ከሰውነት ተራ እስኪወጡና ያልፍልናል ብለው የወጣትነት እድሜያቸውን እሮጠው ሳይጠግቡ በአረብ ቤት የቁም እስረኛ ይመስል ታፍነው ከእናታቸውና ከአባታቸው ጉሮሮ ነጥቀው ዘመድኩን የሃይማኖት አስተማሪ ነው ብለው በየዋሕነት አምነው የሰጡትን ገንዘብ ነው ሰብስቦ  የጠፋው።


ልዑል ሰገድ ደግሞ በእነዚህ ምስኪን እህቶች ገንዘብ ያገኘውን መኪና ይዞ በድሆቹ እህቶች ቤተስብ ፊት እየተንደላቀቀ ዛሬም የእመቤታችንን ስም መሸፈኛ አድርጎ በየዓውደ ምሕረቱ እንደ እባብ እየተቅለሰለሰ ያጭበረብራል።

ዘመድኩንን ከሃገር፣ ከቤተሰቡና ከልጆቹ ነጥሎ እንደ ደራሽ ውሃ ወስዶ ከራየን ወንዝ ማዶ የጣለው የእነዚህ የምስኪን እህቶቻችን እንባና ያለስማቸው ክፋ ስም እየሰጠ የሚሰድባቸው አባቶችና የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ሐዘን ነው። ንስሐ ገብቶ የበደላቸውን ሁሉ ይቅርታ እስካልጠየቀ ድረስ ገና እግዚአብሔር አልጋ ላይ ጥሎ በበሽታ ይቀጣዋል።

ንዋይ ካሳሁን የሚባለው አስመሳይ ግለሰብ ደግሞ አዲስ አበባ በሚኖርበት ጊዜ የማህበረ ቅዱሳን ተላላኪ ሆኖ ሲያገለግል  የኖረ በተለይ የግቢ ጉባዔ አስተምራለሁ እያለ በሚሄድባቸው ቦታዎች ሁሉ ሴት ተማሪዎችን በማማገጥ የሚታወቅና ፈጥሮ በሚያወራቸው የውሸት ወሬዎቹ በጓደኞቹ ዘንድ «ንፋተ ቀርን» በሚል መጠሪያ የሚጠራ ሲሆን አሜሪካ ለትምህርት ነው የሄድኩት ብሎ በኋላ ግን የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ መንግስትን እና ቤተክህነትን እቃወማለሁ ብሎ አሳይለም ቢጠይቅም በተለያዩ ጊዜያት ግን በሶሻል ሚዲያ ላይ በስደት ላይ ያሉ ብፁአን አባቶችንና ካህናትን እየተሳደበና በወረዱ ቃላት እያብጠለጠለ የሚገኝ  አጭበርባሪ ሰው ነው። ይህንን ጉዳይ ለሚመለከተው የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የቤተክርስቲያን ልጆች ታሳውቁ ዘንድ ከወዲሁ እንጠቁማለን።     


ብፁዕ አቡነ በርናባስ ከልጅነት እድሜያቸው ጀምሮ የቤተክርቲያንን ትምህርት ከአባቶች እግር ሥር ቁጭ ብለው በመማር ያደጉ፣ በቅኔ፣ በጸዋትወ ዜማ፣ በቅዳሴ ሙሉ እውቀት ያላቸው፤ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ንባቡን ከነትርጓሜው ጠንቅቀው የተማሩ፤ በመጻሕፍተ ሊቃውንት ጥልቅ እውቀት ያላቸው አባት ናቸው። ከቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅም በክብር ተመርቀው በመላ ኢትዮጵያና በዓለም ዙሪያ እየዞሩ ያለመታከት ወንጌልን ሲሰብኩ የኖሩ ታላቅ ሐዋርያ በአረጋዊነት እድሜያቸው እግዚአብሔር የቤተክርስቲያን አባት አድርጎ በሊቀ ጵጵስና ያከበራችው በንጽህናቸውም የተመሰከረላቸው ታላቅ አባት ናቸው።

ለዛሬው ብፁዕ አቡነ በርናባስ ያስተማሩትንና አባይነህና ዘመድኩን ያለ አቅማቸው ገብተው ክህደትና ኑፋቄ ነው ያሉትን የነገር ድኅነት ትምህርት ቀጥለን እናቀርባለን።

ብፁዕነታቸው በትምህርታቸው መሀል ይህንን ነበር ያሉት። « …ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክነቱ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ተማላጅ ነው በሰውነቱ ደግሞ አማላጅ ነው፤ ለምን? እኛን ስለሆነ፤ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት አማላጅም ነው ተማላጅም ነው። ይህ ሲባል ግን ዛሬ ኪሩቤል ላይ ሆኖ እየወደቀ፣ እየተነሳ፣ እያለቀሰ ይማልዳል ማለት አይደለም። በጌቴ ሴማኒ እኔ እና አንተ አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሁኑ ያለው፣ በቀራንዮ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሎ አንድ ጊዜ የጮኽው ለዘለዓለም ሲጮኽ /ሲያስታርቅ/ ይኖራል ለሚያምኑ ደሙ ዛሬም ትኩስ ነው። በመስቀል በተፈጸመው የደኅንነት ሥራም ክርስቶስ በፈራጅነት ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አብሮ ፈራጅ ነው በማን ላይ? በራሱ ላይ፤ በሰውነቱ ደግሞ የተፈረደበት ነው ለእኛ ሲል። ኢየሱስ ክርስቶስ ለአብ ለመንፈስ ቅዱስ መስዋዕት አቅራቢ ነው፣ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበው ደግሞ እራሱን ነው፣ በሰውነቱ መስዋዕት ነው፣ መስዋዕት አቅራቢም ነው፤ በአምላክነቱ ደግሞ እንደ አብ እንደ መንፈስ ቅዱስ መስዋዕት ተቀባይ ነው። በክርስቶስ ማመን ማለት በሌላ አነጋገር በፍቅር ማመን ማለት ነው፤ በክርስቶስ ማመን ማለት በሰላም ማመን ማለት ነው፤ በክርስቶስ ማመን ማለት ይቅር ባይ መሆን፣ ደግ መሆን፣ ቂም ቋጥሮ አለመኖር ማለት ነው። የተጣላችሁ ታረቁ፣ ቸሮች ሁኑ፣ የዋሖች ሁኑ፣ የተራበ አብሉ፣ የተጠማ አጠጡ የታረዘ አልብሱ፣ ለወገን አስቡ ለራሳችሁ ብቻ አትኑሩ፣ ትህትና ይኑራችሁ፣ እግዚአብሔር ሁላችንን ከሞተ ሕሊና ያስነሳን።…» ነበር ያሉት፡፡

እንግዲህ አንባብያን ልብ በሉ ይህ የሊቀ ጳጳሱን ትምህርት ምንፍቅና ነው ያሉት እነዚህ ከእውቀት ነጻ የሆኑና የቤተክርስቲያኒቱን አስተምህሮ ጠንቅቀው ያልተማሩት ተራ ግለሰቦች የቤተክርስቲያኒቱን መጻሕፍት ቢመረምሩና ሊቃውንትን ቢጠይቁ ስለጥፋታቸው አንገታቸውን ደፍተው በዕንባ ንስሐ በገቡ ነበር፤ ነገር ግን በልባቸው የነገሠው ርኩስ መንፈስ ህሊናቸውን አሳውሮ ዛሬም በጥፋታቸው ቀጥለውበታል።

እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ የብፁዕ አቡነ በርናባስ ትምህርት በተለያዩ መጻሕፍት ውስጥ በግልጽ የሚገኝ እና የቀደሙ መንፈሳውያን ሊቃውንት አባቶቻችን በሚገባ ያስተምሩት የነበረ ንጹሕ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ነው።

ክርስቶስ በሥጋው ወራት የፈጸመው ምልጃ ከደኅንነት አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ የሆነና ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ልዩ ፍቅር የገለጸበት መንገድ ነው። ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ከወድቀቱ ሊያነሳውና ወደቀደመ ክብሩ ሊመልሰው የሚችል ተመጣጣኝ ወድ መስዋዕትና በአብ ፊት ሊታይ የሚችል ብቁ ሊቀ ካህን ለዘመናት ተፈልጎ ስላልተገኘ አብ በመልክ የሚመስለውና በባሕርይ የሚተካከለውን ከእርሱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በቃልነት ህልው ሆኖ የሚኖረውን አንድያ የባሕርይ ልጁን በተለየ አካሉ ወደ ምድር ይወርድ ዘንድ ፈቀደ በአንድ ልጁ እስኪጨክንም ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ያለዋጋ ወዶ የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት በልጁ ትከሻ ላይ አኑሩ ዓለሙ ሊቀጣ የሚገባውን ቅጣት ልጁ እንዲወስድ አደረገ። ዮሐ 316 ይህ ፍቅር የሚደንቅ ፍቅር ነው፤ ይህ ጥበብ ከአዕምሮ በላይ ነው፤ እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ እጅግ ይረቃል።

ቅዱሱ የእግዚአብሔር በግ መሲህ ክርስቶስ መለኮትን ከትስብእት ጋር አዋሕዶ በአጭር ቁመትና በጠባብ ደረት በመወሰን በምድራችን ተገለጠ፤ ሕዝብና አሕዛብን በምኩራብና በገበያ፣ በታንኳና በተራራ ላይ ቆሞ ማርና ወተት ከሚያንጠበጥብ ከናፍሩ ፍቅርን ሰበከ፤ በአይሁድ ገመድ ሳይሆን በፍቅር ገመድ ታስሮ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ በደም ላብ ተዘፍቆ ተጎተተ፣ በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ለመታረድም እንደሚነዳ ጠቦት አንገቱን ደፍቶ በደም ያጌጠ ጀርባውን፣ በጅራፍ የተተለተለ ክንዱን፣ በመስቀል የደቀቀ ትከሻውን፣ በእሾህ አክሊል የተሰነጠቀ ገፁን ይዞ በአብ ፊት የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት በራሱ ላይ አኑሮ ለቤዛነት ታየ። መስቀሉ መሰዊያ፣ ሰውነቱ መስዋዕት እራሱ ራሱ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሆኖ በአባቱ ፊት በብርቱ ጩኽት ከእንባ ጋር ምልጃንም አቀረበ፤ ይህ ምልጃ ዓለሙ ሁሉ እንዲድን፣ የባርነት ቀንበር እንዲሰበር፣ እርግማን እና ፍዳ ከምድሪቱ እንዲወገድ የልጅነት ክብርና የወራሽነት ሥልጣን እንዲሁ ያለዋጋ በጸጋ እንዲሰጥ ክርስቶስ ኢየሱስ እየቃተተ አንድ ጊዜ ያቀረበው ነገር ግን ለዘለዓለም ዓለሙን ከእግዚአብሔር ጋር ሲያስታርቅ የሚኖር ምልጃ ነው፤ አብ መንፈሱ የረካበትን የተወደደ መስዋዕት ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አገኘ፤ ለሰዎች በድካማቸው የሚራራ ታማኝ ሊቀ ካህን አሁን ገና አባቱ አየ፤ ልጅ ስለመሆኑም ተሰማለት ይህ ምልጃም አምነው ለተቀበሉት ሁሉ ለዘለዓለም የመዳን ምክንያት ሆነላቸው። መጽሐፍ እንዲህ ይላል «እርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኽትና ከእንባ ጋር ጸሎትና ምልጃን አቀረበ እግዚአብሔርንም ስለመፍራቱ ተሰማለት ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለተጠራ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘለዓለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።» ዕብ 57

ይህ የክርስቶስ የማስታረቅ ሥራ አንድ ጊዜ ተፈጽሞ ነገር ግን ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ዓለምን ሲያድን የሚኖር ጽድቃችን ነው። በእርሱ አምነው ለተጠመቁና ክርስቶስ ሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብለው በእምነት ለሚመሰክሩ ሁሉ ወደ አባቱ ርስት የሚገቡበት በደም ተመርቆ የተሰጠ የአዲስ ኪዳን የእርቅ መንገድ ነው።

ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል «እርሱ ግን ለዘለዓለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።» ዕብ 723

ወድ አንባብያን ክርስቶስ ዛሬ በሰማያት በግርማው ዙፋን በክብር አለ ዛሬ ላይ ማርልኝ፣ ይቅር በልልኝ እያለ የሚወድቅ የሚነሳ ጌታ አይደለም ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በክብር ተካክሎ ይፈርዳል እንጂ፤ ነገር ግን በዕለተ አርብ በቀራንዮ መካን የፈጸመው ምልጃ ዓለም እስክታልፍ ድረስ በክርስቶስ ቤዛነት አምነው የሚቀርቡትን ሁሉ ሲያስታርቅ ይኖራል።
«
እርሱም እንደነዚያ ሊቀ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መስዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጓልና።» ተብሎ ነው የተጻፈው ዕብ 727

በቀራንዮ መስቀል ላይ የፈሰሰው የክርስቶስ ደም ዛሬም ድረስ ትኩስ ሆኖ የሚያስታርቅ ደም ነው እንጂ እንደ በጎችና ፍየሎች ደም አፈር በልቶት የሚቀር ምውት ደም አይደለም። መጽሐፈ ቅዳሴ እንዲህ ይላል «ወናሁ ደመ መሲህከ ንጹህ ዘተከዕወ በእንቲአየ በቀራንዮ ይኬልሕ ህየንቴየ ዝንቱ ደም ነባቢ ይኩን ሰራዬ ኃጢአትየ ለገብርከ» «ስለ እኔ በቀራንዮ የፈሰሰ ንጹህ የሚሆን የመሲህም ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮኻል ይህ የሚናገር ደም የእኔን የባሪያህን ኃጢአት የሚያስተሰርይ ይሁን።» ቅዳሴ ሐዋርያት አንቀጽ 106
የክርስቶስ ደም ከአቤል የተሻለ ደም ነው የአቤል ደም ተበቀልልኝ እያለ ለዘመናት ከምድር ወደ ጸባዖት ይጮኽ ነበር የክርስቶስ ደም ግን እስከ ዕለተ ምጽዓት ማርልኝ እያለ የሚጮኽ ደም ነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ «የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሚሆን ወደ ኢየሱስ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መረጨት ደም ደርሳችኋል» ያለው ዕብ 1224 የሚሻለው ንግግር ምንድነው? ቢባል ምሕረትን ሲጠይቅ ለዘለዓለም መኖሩ ነው።

አሁንም በመጽሐፈ ቅዳሴ ላይ ጥንታውያን አባቶቻችን ያስቀመጡልን እንዲህ የሚል ጸሎት አለ «ወልድ ሆይ እንደታመመ ሰው አሰምተህ ተናገር ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ በል፣ በአፋቸውም ውስጥ ሳለ አባ አባቴም ሆይ ሥጋዬን የበሉትን ደሜንም የጠጡትን ማራቸው ይቅር በላቸውም በል» ይላል መጽሐፈ ቅዳሴ (ቅዳሴ አትናቴዎስ አንቀጽ 144)

ታላቁ የቤተ ክርስቲያን አባት ቅዱስ ዮሓንስ አፈወርቅም እንዲህ ብሏል «ወጊዜ ፈቀደ ይተንብል ሎሙ አኮ በዝንቱ ጊዜ ባሕቲቱ፣ አላ በእንተ ዘትመጽዕ ሕይወት ዘለዓለም» «በወደደ ጊዜ ይለምንላቸዋል በዚህ ጊዜ ( በዕለተ አርብ ) ብቻም አይደለም ከዚያም በኋላ ባለው ጊዜ ለዘለዓለም ነው እንጂ» ሃይማኖተ አበው ገፅ 208(1987) ወይም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዕብራውያንን መልእክት በተረጐመበት 13 ድርሳኑ ቊጥር 156

ክርስቲያን ወገኖቼ ልብ በሉ እግዚአብሔር "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት" ብሎ አንድ ጊዜ የተናገራት ቃል ሕያው ሆና ሁሌም ትውልዱን በዘር ስትባርክ እንደምትኖር ሁሉ ክርስቶስም በምድር ሳለ አንድ ጊዜ "ይቅር በላቸው" ብሎ የማለዳት ምልጃ ለዘለዓለም ሕያው ሆና በክርስቶስ ስም አብን ለሚማጸኑ ሁሉ ይቅርታን ስታሰጥ የምትኖር ሕያው ቃል ነች። እንዲህ በሚደንቅ ፍቅርና ጥበብ የመዳን በር የሆነን ክርስቶስ ስሙ ለዘለዓለም ከፍ ከፍ ይበል።

ታላቁ የቤተክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ አባት ቄርሎስ እንዲህ ይላል «ወሰአሎ ለአብ ያኅልፍ እምኔነ መዐተ ዘረከበነ እምቅድም ከመ ዘለሊሁ ይኌልቊ ስእለተ ሎቱ እስመ ውእቱ ነሥአ አምሳሊነ ከመ ይስአሎ ለአብ በእንቲአነ ከመ ምዕረ ዳግመ ይዝክረነ ወኢይኅድገነ እምኔሁ።» «እርሱ ለራሱ ልመናን የሚሻ መስሎ ከጥንት ጀምሮ ያገኘንን ፍዳ ከእኛ ያርቅ ዘንድ አብን ማለደው እንደገና ደግሞ እንዲያስበን ከእርሱም እንዳይለየን ስለ እኛ አብን ይማልደው ዘንድ ባህርያችንን ነስቷልና።» ሃይማኖተ አበው ገጽ 124 (1986) ወይም (ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 79 ክፍል 50 ቊጥር 38)

አሁንም በዚሁ በሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ላይ ታላቁ አባት ቅዱስ ዮሓንስ አፈወርቅ በድጋሚ እንዲህ ይላል «መኑ ውእቱ ሊቀ ካህናት ወምእመን ዘእንበሌሁ ዘይክል ለሊሁ ባህቲቱ ሰራዬ ኃጢያት ወምንት ውእቱ መሥዋዕት ዘአዕረጎ በእንተ ዝንቱ ሥርዓት ዘእንበለ ሥጋሁ ባህቲቱ ዘነስአ በእንተ ዘንቱ ግብር»
«
ከእርሱ በቀር ራሱ ብቻውን ኃጢአትን ማስተስረይ የሚቻለው የታመነ አስታራቂ ማነው? ለማስታረቅ ኃጢአትን ለማስተስረይ ያቀረበው መስዋዕትስ ምንድነው? መስዋዕት ለመሆን የነሳው ሥጋው ብቻ ነው እንጂ ... እርሱ ወደዚህ ዓለም ወርዶ ባህርያችንን ባህርይ አድርጎ ሊቀ ካህናት (አስታራቂ) ሆነን።» ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ ምዕ.631416

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በመጽሐፈ ሰዓታት ድርሰቱ ላይ እንዲ ይላል «ሊቀ ካህናት ዘይቀውም ሎሙ ለቅዱሳን በደብተራ ስምዕ እንተ እግዚአብሔር ተከላ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ።» «እግዚአብሔር በተከላት በምስክር ድንኳን (ሰማያዊት ቤተመቅደስ) ውስጥ የሚቆመው ሊቀ ካህናት እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።»

የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ሐዋርያዊት የሆነች ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን እንዲህ የጠራና ግልጽ የሆነ አስተምህሮ አላት ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ይህ አስተምህሮ እንግዳ ትምህርት እየመሰላቸው ግራ ሲጋቡ እናያለን መጻሕፍትን መመርመር እና የተማሩ አባቶችን መጠየቅ ግን የእኛ ድርሻ ነው ክርስቶስ በዕለተ አርብ የፈጸመው የማስታረቅ አገልግሎት ዛሬም ድረስ መማጸኛችን እና መታረቂያችን ነው። ይህን ስንል ደግሞ የቅዱሳን ቃል ኪዳንና ጸሎት አያስፈልግም ማለት አይደለም። ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ንቀው በገድል በትሩፋት የዲያብሎስን ሐሳብና የሥጋን ፈቃድ ድል ነስተው የመስቀሉን መከራ በልባቸው ሰንቀው የክብሩን ወንጌል ለዓለም በመስበክ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ፍቅር ያስመለጡ የመንግስተሰማያት ጃንደረቦች ጻድቃን ሰማዕታት ጸሎታቸው ከክርስቶስ ጋር ሕብረትን እንድንፈጥር ይራዳናል። አንባቢ አስተውል መንግስተ ሰማያት መግቢያ ብቸኛው መንገዳችን ግን ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው፤ ነገር ግን የሞተልንን ጌታ በኃጢአትና በርኩሰት በደም ማፍሰስ እና በጣዖት አምልኮ አሳዝነን ከመስቀሉ ጥላ ሥር ከራቅን በኋላ በንስሐ ስንመለስ በፍጹም ጸጸት፣ በጾም፣ በጸሎት፣ ይቅርታ እየጠየቅንና በቅዱሳን ጸሎትና ቃልኪዳን እየተማጸንን ከክርስቶስ ጋር እንታረቃለን እረፍትና ሕይወትንም በእርሱ በኩል እናገኛለን።

እንግዲህ ልብ በሉ ይህንን በመጽሐፍት ምስክርነት ላይ የተመሰረተውን ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ነው የማህበረ ቅዱሳን ጆቢራዎች በሌላቸው እውቀትና መረዳት ምንፍቅና ነው እያሉ ትውልዱን ስተው እያሳቱ ያሉት እንዲህ ዓይነት የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርት የሚያስተምሩ አባቶችንና መምህራንን ማህበረ ቅዱሳን ለ20 ዓመታት እያሳደደ በቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ቆመው እንዳይሰብኩ እያሳደመ ዛሬ ቤተክርስቲያን ከ10 ሚሊየን በላይ አማኞቿን እንድታጣና ወደ ሌሎች ቤተ እምነቶች እንዲፈልሱ አስደርጓል፤ ጅራፍ እራሱ መቶ እራሱ ይጮኻል እንደሚባለው ዛሬ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እያሉ ገንዘብ ለመሰብሰብ በየቦታው ተከፋፍለው በፕሮጀክትር ለሕዝብ በሚሰጡት ትምህርት ሕዝቡ እንዲፈልስ ያደረጉት ተሐድሶዎች ናቸው እያሉ ሕዝቡን ግራ ያጋቡታል እንጂ  አገልጋዮቹን ግን ከቤተክርስቲያን በግፍ ዱላ አሳዶ ቤተክርስቲያኒቱን የወላድ መኻን እያደረጋት ያለው ይሄው የንግድና የፓለቲካ ማህበር ማህበረ አጋንንት ማቅ ነው። እግዚአብሔር አምላክ አባቶቻችንና እውነተኛውን ወንጌል ገልጸው የሚነግሩንን መምህራንን የምናዳምጥበትን አስተዋይ ልቡና ለሁላችን ይስጠን።
ከሳሙኤል

13 comments:

 1. enante ye effugnit lijoch. ahununu medenin feligu, Tiwulidin eyenekesachu eskemeche tinoralachu!!!!!! enante ke sirachu tawukobachihual. ewunetin yeyazut mahibere kidusanin, Muaze
  tibebat DN Daniel Kibretinim, Mr Zemedkunim, Dn ABayneh Kasem.....lylochim egna sirachewunim Yesirachwenim fre enawuqalen!!!!!!!!!!! Enante wushoch, wushetamoch, lyboch!!!!!

  ReplyDelete
 2. መማርን ለሳቸው ብቻ የሰጠሃቸው; እሳቸው ከአገር ከወጡ በኇላ መምህራኑ እሳቸው ከሌሉ አናስተምርም ብለው ወንበር አጠፉን:: እስኪ ስለትምህርታቸው ንገሩን::

  ReplyDelete
 3. ሳሙኤል፣ ስለ ጽሑፉ እግዚአብሔር ይባርክዎ፡፡
  የኢየሱስን መካከለኛነት፣ አማላጅነት አለመቀበል ማለት “ቃል ሥጋ ኾነ” የሚለውን መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚቃረን ክሕደት ነው፡፡ “ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል (በዐረቢኛ ከሊማቱላህ) እንጂ አምላክ አይደለም፤ ሰው ቢኾንም አልተሰቀለም” ከሚለው መሐመዳዊነት ቢብስ አይሻልም፡፡ አዎን! ጌታችን ኢየሱስ ምትክ የሌለው፣ አማራጭ የማይበጅለት አማላጃችን፣ ጠበቃችን፣ ዋሳችን፣ መካከለኛችን ነው፡፡ ይኼን የማይቀበል ክርስቲያን ነኝ ሊል አይችልም፡፡
  ይኹን እንጂ፣ በጽሑፍዎ ውስጥ የተመለከትኹት እግዚአብሔር አብ በልጁ ትከሻ ላይ “የዓለምን ሁሉ ኃጢኣት አስቀምጦ ዓለሙ ሊቀጣ የሚገባውን ቅጣት ልጁ እንዲወስድ አደረገ” የሚል አስተምህሮ ደግሞ እኔ እስከማውቀው ድረስ ከቤተ ክርስቲያን አበው አንደበት የለም፡፡ “የኹላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ” የሚለውን የኢሳይያስን ቃል በዚኽ መንገድ ካነበብነው እግዚአብሔር አብን (ሎቱ ስብሐት!) ደም የጠማው የአሕዛብ ጣዖት እናስመስለዋለን፡፡ እንዲኽ ያለውን የነገረ ድኅነት ትንተና በተለይ የኢቫንጄሊካልስ ተብለው የሚጠሩ የክርስትና ቡድኖች ይጠቀሙታል፡፡ ይኽ ግን ፍጹም ስሕተት ነው!
  የኢየሱስ አስታራቂነት መስቀሉ ላይ ብቻ አይደለም፡፡ ከፅንሰት እስከ ቀራንዮ፣ ከጎልጎታ እስከ ዕርገት ድረስ እንጂ- አበው የሚያስተምሩት እንዲኽ ነው፡፡ በኃጢኣት ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለይቶ ሞቶ የነበረው የሰው ልጅ መላ እርሱነቱ ዕርቅን ይፈልግ ነበር፡፡ ስለዚኽም የእግዚአብሔር ቃል ሰው መኾንን ወደ ቀደመ ክብሩ ሊመልስ ሰው ኾነ፡፡
  በፅንሰቱ ሰው ኾኖ መፀነስ ክቡር የአምላክ ገንዘብ ኾነ፡፡ በልደቱ ሰው ኾኖ በዚኽ ምድር ላይ መወለድ አምላክን መምሰል ኾነ፡፡ ሰው ኾኖ በየጥቂቱ ማደግ የእግዚአብሔር ልጅ የኼደበት እኛም እርሱን የምንመስልበት የሕይወት ጎዳና ኾነልን፡፡ መብላት መጠጣትን፣ መተኛት መነሣትን ኹሉ የእግዚአብሔር ልጅ ገንዘቡ አደረገልንና ክቡር ኾኑ፡፡ በሞቱ ሞታችንን ረገጠው፡፡ በትንሣኤው ትንሣኤያችንን አበሠረን፡፡ በዕርገቱ ከኪሩቤል ከፍታ በላይ ከፍ አደረገን፡፡ ዳግመኛም ለምንጠባበቀውም- የዕብራውያን መልእክት እንደሚነግረን- ኹለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢኣት ይታይልናል (ይገለጥልናል/ ይመጣልናል)፡፡ እንዲኽ የወደደንን ምን እንላለን? ክብር ይግባው!ቅዱስ ጳውሎስ “አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ራሱን ስለእኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው” አለ (ገላ 2፡ 20)፡፡ አኹን ሰው መኾን የእግዚአብሔር ልጅ ገንዘቡ ነው፡፡ ስለዚኽም ትልቅ ጸጋ ተሰጥቶናል፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሚወድደን፣ ዕቅፉ የሚሰበስበን፣ ሕይወቱን ያካፈለን ወንድማችን ኾኖልናልና፡፡ በዚኹም ግን ታላቅ ፍርድ ወድቆብናል፤ የእግዚአብሔርን ልጅ ገንዘብ (በዚኽ ምድር ላይ ሰው ኾኜ የምኖረውን ሕይወት) ለክብሩ ካልኖርኹት፣ የዓይን አምሮትና የሥጋ ፍላጎቴን እየተከተልኹ ባረክሰው ፍርድ ይጠብቀኛል፡፡ ፍጹም ጸጋ! ፍጹም ፍርድ! አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ “ሰው አምላክ ይኾን ዘንድ አምላክ ሰው ኾነ” ይላል፡፡ የአምላክ በመኾን በጸጋው አምላክ መኾንን ካልመረጥኹ መጨረሻዬ የጨለማው ኃይሎች ገንዘብ በመኾን እግዚአብሔርን በመጥላት ጨለማ ውስጥ ከአጋንንት ጋር ለዘለዓለም ጋኔን መስሎ መኖር ነው፡፡
  ይኽ አኹን የምናየው- ከፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ መጀመር በኋላ የተስፋፋ ጎደሎ የነገረ ድኅነት አስተምህሮ- መስቀሉ ላይ ብቻ የሚያተኩር የነገረ ድኅነት ትንታኔ ኢየሱስ ለምን እንደሞተ እንጂ ለምን እንደኖረ አያሳየንም፡፡ አበውም እንዲኽ አላስተማሩም፡፡ እግዚአብሔር አብ ግን ከፍቅሩ የተነሣ ልጁን የላከልን የሚወድደን አባታችን እንጂ በሥራችን ከመናደዱ የተነሣ ሊገድለን ይፈልግ የነበረ ጠላታችን አይደለም፡፡
  ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ በፋሲካ ስብከቱ ይኽን አስመልክቶ እንዲኽ ይላል፡-
  We must now examine the question and the dogma so often passed over in silence, but which (I think) demands no less deep study. To whom was that blood offered that was shed for us, and why was it shed? I mean the precious and glorious blood of God, the blood of the High Priest and of the Sacrifice? We were in bondage to the devil and sold under sin, having become corrupt through our concupiscence. Now, since a ransom is paid to him who holds us in his power, I ask to whom such a price was offered and why? If to the devil it is outrageous! The robber receives ransom, not only from God, but a ransom consisting God Himself. He demands so exorbitant a payment for his tyranny that it would have been right for him to have freed us altogether. If the price is offered to the Father, I ask first of all, how? For it was not the Father who held us captive. Why then should the blood of His only begotten son please the father, who would not even receive Isaac when he was offered as a whole burnt offering by Abraham, but replaced the human sacrifice with a ram? Is it not evident that the Father accepts the sacrifice not because He demanded it or because He felt any need for it, but on account of economy: because man must be sanctified by the humanity of God, and God Himself must deliver us by overcoming the tyrant through his own power, and drawing us to Himself by the mediation of the Son who effects this all for the honor of God, to whom He was obedient in everything. … what remains to be said shall be covered with reverent silence.

  ReplyDelete
 4. እኔ ደግሞ ሊቁ አቡነ በርናባስ ስትል ሌላ ሰው መስሎኝ ደንግጬ ውስጡን ሳየው ሰውዬው አባ ወልደተንሳይ ሆነው እርፍ:: ሊቅነታቸውን ማን ካደ ችግሩ ዘመዳቸው አርዮስስ ሊቅ ነበር ይባላል:: እውቀት የሚያድነው እምነትና ፈሪሃ እግዚአብሄር ሲታከልበት ነው:: እውቀት አለን ብለው እንደው ሲዳፈሩ ከእኛ ሰፈር ርቀው ተገኝተዋል:: እውቀት በዝቶ የሚሰበክ ጠፋና ቅማል ብሉ ብለው ያረፉትም ሰውዩ አይደሉ:: ወይ ጉድ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔ ደግሞ ሊቁ አቡነ በርናባስ ስትል ሌላ ሰው መስሎኝ ደንግጬ ውስጡን ሳየው ሰውዬው አባ ወልደተንሳይ ሆነው እርፍ:: ሊቅነታቸውን ማን ካደ ችግሩ ዘመዳቸው አርዮስስ ሊቅ ነበር ይባላል:: እውቀት የሚያድነው እምነትና ፈሪሃ እግዚአብሄር ሲታከልበት ነው:: እውቀት አለን ብለው እንደው ሲዳፈሩ ከእኛ ሰፈር ርቀው ተገኝተዋል:: እውቀት በዝቶ የሚሰበክ ጠፋና ቅማል ብሉ ብለው ያረፉትም ሰውዩ አይደሉ:

   Delete
 5. አይገርምም ያንተ ጆቢራዎች ቀስ በቀስ ተመነገሉ

  ReplyDelete