Tuesday, August 29, 2017

በማኅበረ ቅዱሳን አማካይነት በወንጌል ላይ የተከፈተው ፀረ ወንጌል ዘመቻ
የተሐድሶ እንቅስቃሴ ከጫፍ የደረሰ ይመስላል ጸረ ወንጌል ቡድኖች የወንጌል እውነት የተላለፈባቸውን መጻሕፍትና የመዝሙር ሲዲዎች ማቃጠል ይዘዋል ከዚህ ቀደም በሻሸመኔ አሁን ሰሞኑን ደግሞ በድሬዳዋ ይህን አስመልክቶ ኤልጃይስ የተባለ ወንድም በፌስ ቡክ የለጠፈውን ጽሁፍ እናስነብባችሁ፡፡

ይድረስ፤ ለተወደድከው ወንድማችን ዳንኤል ክብረት
Daniel Kibret Daniel Kibret Blog Daniel Kibret Views
ወንድማችን ዳንኤል ክብረት፤ ሰላምና ጤና በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለአንተ ይሁን፡፡ (ዳኒ፤ ዲያቆን፣ ሙሃዘ ጥበባት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛው ተመራማሪ የሚሉ የማዕረጋት ስያሜዎችህን መጠቀም ባለመፈለጌ፤ ከልብ ይቅርታ እጠይቅሃለሁ)፡፡ ዛሬ ስምህን እንድጠራ ያስገደድኝ ነገር ሰሞኑን በድሬደዋ የፈጸማችሁት አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ ለዚህችም አጭር ጡመራዬ ምላሽህን እጠብቃለሁ፡፡ አንተ የደራሲያን ማኅበራት ላይ አለው አለው የምትል ግለሰብ ስትሆን፤ የፈጸምከው ድርጊት በጣም አስተዛዛቢ ነው፡፡ ዳኒ አንተ እኮ ባገኘሁ ሚድያ ሁሉ፤ ለደራሲያን መብት እቆማለሁ፣ ለፕሬስ ነጻነት እሟገታለሁ የምትል ግለሰብ፤ እንዴት ባለ አዕምሯዊ እሳቤ ብትነሳ ነው የሰው አዕምሮ ውጤት የሆኑ ዝማሬዎችን፣ መጻሕፍትን፣ ስብከቶችን፣ ቪሲዲዎችን፣ የኅትመት ውጤቶችን በአደባባይ ለማቃጠል የተነሳኽው? ይህ በእውነት ከአንተ ይጠበቃል ዳኒ?

Thursday, August 17, 2017

ኢትዮጵያ፥ እግዚአብሔር በደህና ጊዜ የሸጣት አገር“የሃይማኖት አገር!” የሚለው አባባል ኢትዮጵያ ውስጥ ጊዜው ያለፈበትና የተበላ ተረት ሆኖዋል። አጥር ተሳልሞ የሚመለስ፣ ዕሮብና ዓርብ ራሱን ጥሉላት ከሆኑ የምግብ ዓይነቶች ከልክሎ ሲያበቃ ምላሱ የሰው አጥንት ስታደቅ ጸሐይ የምትጠልቅበት፣ ዛሬ ቅድስት አርሴማ ናት ነገ አቡነ ሐራ ነው እያለ ሲኖዶስ የማያውቃቸውን ስሞች እየጠራና ቀናት እየቆጠረ አብያተ ክርስቲያናትን የሚያሳድድ፤ መቼ ይሄ ብቻ - እሁድ በመጣ ቁጥር በክራባት ታንቆ ሲዘምርና “ሲያመልክ” እንደ ቦይንግ 767 ክንፉን ዘርግቶ የሚዘል፣ በቀን አምስት ጊዜ እየታጠበ ሶላት ለማድረስ ወደ መስጅድ የሚመላለስ፣ ቁጥር በክትባት መልክ በቀበሌ የተሰጠ ይመስል ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ቤተ እምነቶች የሚመላለስ ሃይማኖተኛ ዜጋ ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።  
ኢትዮጵያ ውስጥ “ሃይማኖት አልባ” በተለምዶ “ከሃዲ” የሚባለውና በባህላችንም መሰረት በየትኛውም መልኩ ተቀባይነት የሌላው፣ በጋራ ተሰባስበው የሚወያዩበት “ማዕከል” ቀርቶ “ሃይማኖት አልባ/ከሃዲ” ግለሰብን (ሃይማኖት አልባ ግለሰብ የሞራል ኮምፓስ የለውም እያልኩ አይደለም። የ“ሃይማኖት አልባ” ዜጎች ቁጥር ማነስ  ቆጭቶኝም አይደለም) ወይም ሰውን በኩራዝም ቢሆን ፈልጎ ማግኘት ቀላል አይደለም። ቀለል ባለ አማርኛ - ኢትዮጵያ ውስጥ የአንድ ሺህ ሰው እጅ ለመጨበጥ አጋጣሚውን ያገኙ እንደሆነ ከጨበጡት እጅ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኙ ከራሱ በላይ በሆነ “ፈጣሪ አለ” ብሎ በመለኮታዊ ሃይል “የሚያምን” ህዝብ ነው። በአንጻሩ ምድሪቱ ከሙስና የተነሳ እየተናጠች ሳይ ደግሞ - “ኢትዮጵያ፥ እግዚአብሔር በደህና ጊዜ የሸጣት አገር” አስብሎኛል።