Tuesday, August 29, 2017

በማኅበረ ቅዱሳን አማካይነት በወንጌል ላይ የተከፈተው ፀረ ወንጌል ዘመቻ
የተሐድሶ እንቅስቃሴ ከጫፍ የደረሰ ይመስላል ጸረ ወንጌል ቡድኖች የወንጌል እውነት የተላለፈባቸውን መጻሕፍትና የመዝሙር ሲዲዎች ማቃጠል ይዘዋል ከዚህ ቀደም በሻሸመኔ አሁን ሰሞኑን ደግሞ በድሬዳዋ ይህን አስመልክቶ ኤልጃይስ የተባለ ወንድም በፌስ ቡክ የለጠፈውን ጽሁፍ እናስነብባችሁ፡፡

ይድረስ፤ ለተወደድከው ወንድማችን ዳንኤል ክብረት
Daniel Kibret Daniel Kibret Blog Daniel Kibret Views
ወንድማችን ዳንኤል ክብረት፤ ሰላምና ጤና በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለአንተ ይሁን፡፡ (ዳኒ፤ ዲያቆን፣ ሙሃዘ ጥበባት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛው ተመራማሪ የሚሉ የማዕረጋት ስያሜዎችህን መጠቀም ባለመፈለጌ፤ ከልብ ይቅርታ እጠይቅሃለሁ)፡፡ ዛሬ ስምህን እንድጠራ ያስገደድኝ ነገር ሰሞኑን በድሬደዋ የፈጸማችሁት አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ ለዚህችም አጭር ጡመራዬ ምላሽህን እጠብቃለሁ፡፡ አንተ የደራሲያን ማኅበራት ላይ አለው አለው የምትል ግለሰብ ስትሆን፤ የፈጸምከው ድርጊት በጣም አስተዛዛቢ ነው፡፡ ዳኒ አንተ እኮ ባገኘሁ ሚድያ ሁሉ፤ ለደራሲያን መብት እቆማለሁ፣ ለፕሬስ ነጻነት እሟገታለሁ የምትል ግለሰብ፤ እንዴት ባለ አዕምሯዊ እሳቤ ብትነሳ ነው የሰው አዕምሮ ውጤት የሆኑ ዝማሬዎችን፣ መጻሕፍትን፣ ስብከቶችን፣ ቪሲዲዎችን፣ የኅትመት ውጤቶችን በአደባባይ ለማቃጠል የተነሳኽው? ይህ በእውነት ከአንተ ይጠበቃል ዳኒ?


እውነት ነው ሰብስባችሁ ያለምንም ገላጋይ ያጋያችኋቸውን ዝማሬዎች፣ የኅትመት ውጤቶች፣ ቪሲዲዎችና መጻሐፍቶችን እንደማትቀበሏቸው የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን አንድን የኅትመት ውጤት ባለመቀበልና በመጥላት መሰረት ብቻ ቆሞ በአደባባይ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ድርጊት መፈጸም ወንጀል እንጂ ጽድቅ አይደለም፡፡ የቀደሙ አባቶቻችንም ሐሰትን በእውነት ሲረቱ እንጂ እንደእናንተ አልተልፈሰፈሱም ነበር፡፡ ታሪካቸው ዛሬም ድረስ ለእኛ ሕያው ምስክር ሆኖ የቆመ ነው፡፡ እነ ቅዱስ አትናቴዎስ፣ እነ ቅዱስ ቄርሎስ፣ እነ ቅዱስ ኤጲፋኔዎስ፣ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሐሰት ትምህርትን እያሳደዱ በሰልፍ ለማጥፋት ሲባዝኑ ሳይሆን የምናውቃቸው በእውነት ቃል ሲረቱ ነው የምናውቃቸው፡፡ እናንተ ግን በእውነት ከየት ነው በቀላችሁ? በውኑ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እንዲህ አስተማረቻችሁን? መንፈሳዊ አባቶቻችሁ እነማን ናቸው? አዎን፤ በርግጥ አባታችሁ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ነው፡፡ የግብር አባታችሁ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ የቀደሙ አባቶቻችንን እነ ቅዱስ እስጢፋኖስንና ደቂቀ እስጢፋኖስን በእውነት ቃል ሳይሆን ሞግቶ የረታቸው በሰይፍ ነው ያስጨፈጨፋቸው፡፡ በእሳት ነው የገደላቸው፡፡ በንፍር ውሃ ነው የቀቀላቸው፡፡ ይገርምሃል፤ በስጋ ቢሞቱም የእነርሱ ልጆች ዛሬ ምድሪቷን ሞልተን ከድነናል እንጂ አንዳች ስንኳ አልጠፋንም፡፡ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ነገም እንበዛለን፡፡
ደግሞስ የአንድን አስተምህሮ ሥህተትና ምንፍቅና መከላከልና ማጥፋት የሚቻለው በዚህ ዓይነት አሳፋሪና የወረደ ድርጊት ነውን? አዕምሯዊ አስተሳሰብን፣ ልባዊ እምነትን፣ በማቃጠል ሕግ በውኑ ማጥፋት ይቻላልን? ይህ ከንቱ ድካም መሆኑን ለማሳወቅ የግድ የሒትለርን ታሪክ ማስታወስ አይጠበቅብንም፡፡ ሐሰትን በእውነት ነው የምትረታው እንጂ በልፍስፍስ ግብር አይደለም፡፡ ክርስትናን በሰይፍ ለማጥፋት መሞከር የልፍስፍሶችና የደካማዎች መገለጫ ነው፡፡ አታስታውስም እንዴ ከክርስቶስ ዕርገት ማግስት በኋላ የተነሳው፣ ክርስትናን በሰይፍ ብዛት ለማጥፋት ብሎ የደከመውን ታላቁን ገዳይ ኒግሮን አታስታውስም? ይገርምሃል፤ ኒግሮ ሞቷል - ኢየሱስና የኢየሱስ ተከታዮች ግን ዛሬም ድረስ በድል አሉ፡፡ ምነው በየስፍራው የምታነሳቸው፤ የእነ ቅዱስ ቶማስ ዘመራስ ታሪክ በራሱ አዕምሮህ ላይ አይቃጭልም? በውኑ ቶማስን የእጁ መቆረጥ ከክርስትና መለሰው እንዴ? የቶማስ እግር መቆረጥ ክርስቶስን ከመከተል አቆመው እንዴ? አላቆመውም! ምክንያቱም የክርስቶስ ሕይወት የታተመው በልባችን መቅዱስ እንጂ በእጅና በእግራችን ላይ ስላልሆነ ነው፡፡ ምናልባት ቶማስን ከክርስትና መመለስ የሚቻልበት መንገድ አንድ ነበር፤ እርሱም በልቡ ያከበረውን እውነት በመሞገትና በማሳመን ብቻ ነው፡፡ ቶማስ ግን ከሚያወጣው የእውነት ቃል የተነሳ የተቋቋመው አንዳች ሰው ስላልነበር ነው የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ወደ እግር ቆረጣ የገቡት፡፡ አንተም ‹‹ካሴትና ቪሲዲ›› ሰብስበህ በማቃጠል እውነትን ከቶ ልታጠፋው አትችልም፡፡ የኅትመት ውጤቶችን አቃጥለህ የምትለውጠው አንዳች ትርፍ አይኖርህም! ይሄን አንተም እኛም በሚመጡ ዘመናት እናያለን፡፡ ግን ለምን ይመስልሃል ክርስትና በሰልፍና በሰይፍ የማይጠፋው? አየህ ዳኒ፤ ክርስትና የቆመው በክርስቶስ ላይ ስለሆነ፤ በስይፍ አታጠፋውም፣ በእሳት አታቃጥለውም፣ በንፍር ውሃ ቸልሰህ አታደፍነውም! እውነት እውነት እልሃለሁ፤ እውነትን ማጥፋት አትችልም፡፡ ይሄን የልቤ ንጉስ በሆነው በጌታዬ በኢየሱስ ስም አረጋግጥልሃለሁ!
ጸጋና ሰላም ይብዛልህ!
አክባሪህ ወንድም ኤልጃይስ!

22 comments:

 1. He is Dani who are you yehonik achiberbari we didn't set fire on nobody's property but on our garbage/yemenafikan bad seed/ which we payed our own hard earned money

  ReplyDelete
 2. በጣም ያሳዝና ለክርስትናውና ለክርስቶስ አስበህ ጠጨንቀህ ሳይሆን ብር ለሚለግሱህ አካላት የገባኸውን ቃል በቅጽበት ባላሰብከው መንገድ ስለፈረሰብህ፤ ስለከበደብህና ብሩና ጥቅማጥቅሙ ይቆማል ብለህ ሰግተህ የምታለቅስ ይመስላል፡፡ በቀጣይ ዘመናት አይሳካልህም አትልፋ

  ReplyDelete
 3. የአእምሮ ምንጭነቱ ከንቱ የሚሆነው በሌሎች ቤት በመገኘቱ ነው ። ባዳራሻቸዉ ቢያደርጉት ማንም አይነካቸውም። ጎበዝ እናስብ እንጂ ገርፎ ከቤቱ ሲያሶጣ ጌታ መጋረፍ የባህሪዉ ሆኖ አይደለም ። ሸቃጮች በቤቱ ስለገቡነዉ ለዛውም ተመሳስለው።

  ReplyDelete
 4. ራስህን በአውሮፓዊ ማንነት ደብቀህ ኢትዮጵያዊ መስለህ ለመደናገር የቆም አስመሳይነህ በመቀጠል አንተና መሰሎችህ እራሳችሁን ሆናችሁ እንደመቆም ለምን መስላችሁ እንደምትኖሩ አይገባኝም ዲያቢሎስም አዳምንና ሄዎንን ለማሳሳት በእባብ ተሰውሮ ገብቶ ነው ከገነት እንዲወጡ የሆነው እናም ማንነተችሁን አውጡና በይፋ ተንቀሳቀሱ ማንም አያገባውም ነገር ግን ከእኛ ሆናችሁ የኛ ያልሆነውን አስገባችሁ ምዕመኑም በየዋህነት ተቀበላቸሁ ነገርግን እውነቱን ሲያቅ የረሱ ያልሆነውን ሲዲም ሆነ ሌላ ማቃጠል ጀመር ይሄ የመጀመሪያው እርምጃ ነው በሃይማኖቱ ማንም ወደኃላ የሚል የለም የዲ/ን ዳንኤል ሥራ እውነተኛውን የእገዚአበሔር ቃል መናገር ነው ምዕመኑ ደግሞ ለይቶ መያዝ ነው ክብር ለሚገባው ክብረ ስጡ የተቃጠሉት በክብር የሚያዙ ስላልነበሩ ተቃጠሉ አከተመ፡፡

  ReplyDelete
 5. ወደድክም ጠላህም ገለባው ከዘሩ መለየት አለበት፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትም ያደረገው ይህንን ነው፡፡

  ReplyDelete
 6. ተነቃባችሁ እናንተ እርኩስ ሀራጥቃ ሁላ፡ ካሁን በሇላ ማንም አይሰማችሁም፡፡ ገለባው ከዘሩ መለየት አለበት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትም ያደረገው ይህንን ነው፡፡

  ReplyDelete
 7. What do you expect from Daniel Kiseret.
  He is just running like a crazy DOG. Dont worry you will repay it soon. Just wait and see.

  ReplyDelete
 8. Heresy is getting outof peoples heart.

  ReplyDelete
 9. አንተና መሰሎችህ በዚህ ድርጊት እርርር ድብን በሉ እንጂ እኛ አስቀድሞ አሳስታችሁን በገዛ ገንዘባችን ገዝተን እናንተን አወፍረን ራሳችንን ግን ለሞት አገልግሎት ገብረን የነበርንባቸውን ካሴትና መጻህፍቶቻችሁን ማቃጠል ብቻ ሳይሆን እናንተ ራሳችሁም የማትመለሱ ከሆነ በዘመኑ መጨረሻ በሲዖል እሳት እንደምትጋዩ ልብ በል እልሃለሁ፡፡

  ReplyDelete
 10. Eljayis new yalkew simihin..gira yegebah neh lik ende simih. The please of those books and CD is not orthodox church; they came there in wrong place so they are burnt. Their respected place is protestant church...where people are brain washed with so called prophets. We respect God with saints....but you call Jesus and worship your pastors.

  ReplyDelete
 11. አዲስ ዘመንን በዘፈን መዝሙር አንፈልግም የቴዴ አፍሮ ዘፈን ይሻለናል።እነዚህ ከመጡ ጀምሮ ነው እንጂ እኮ ድሮም ዘፈን ነው የሚሻል የነበረው።ዘፈን አዳዲስ ዘፈን።የኦርቶዶክስም መዝሙር ፍጡራንን የሚያወድስ ስለሆነ ከዘፈን አይሻልም።

  ReplyDelete
 12. የገደለ ይገደላል እንደተባለ ማንም ገፊ ይገፋል ማንም አቃጣይ ይቃጠላል ማንም ነገረ ሠሪ ነገር ይሠራበታል። ለግፈኞች ደገሞ እስከሲኦል ማን ይታገሳቸዋል በቁማቸው የጃቸውን ያገኛሉጂ
  ይህም የፈጸሙትና የሚፈጽሙት ግፍ ዕረፍት ይነሳቸዋል እንቅልፍ ያሳጣቸዋል ባንድ ወይም በሌላ አቅጣጫ የቁም ኩነኔ ያገኛቸዋል። አስመሳይ የሀይማኖት ተቈርቋሪዎች ናቸውና እንዲህና ይህን የመሰለ ግፍ በፈጸሙና በሚፈጽሙ አታላዮች ላይ መቻያውን ያመጣባቸዋል።

  ReplyDelete
 13. ጽዋው የሞላ ጊዜ ዲ/ን ዲንኤል ምን ትሆን ይሆን?ትውልድህን ዘርህን ልጆችህን ለምን የመከራ እንጀራ ታቆያቸዋለህ?ምናለበት ዝም ብለህ የታሪክ ነገርህን ብቻ የሚያምረውን ብታደርግ?ሰው በዘመኑ የዘራውን ያጭዳል የሚለውን ታሪክ አጥኝዎች ይቀበሉት ይሆን?በማያገባን ነገር ባንገባ ነገሮችን እኛ እንደምንፈልጋቸው ባናጣምማቸው?ከተጠያቂነት ነጻ ስለማንንወጣ ይሄንን እንደጀብዱ እየቆጠርን እሰይ ከምንል ይህን ሰው ከጥፋት ብንመልሰው እንደተማረ እንዲያስብ የሰለጠነ አእምሮ ላይ የደረሱ ምሁራን ያሉበት ሀገር እዚህ የደረሱት የሰው ሃሳብ እየጨፈለቁ እየደፈጠጡና የራሳቸውን ሃሳብ ሰው ላይ እየጫኑ አይመስለኝምና እስቲ ወደ አእምሮ ወደ ልብ መለስ እንበላ?የእግዚአብሔር ጽዋ የሞላ ለት ወየውልን?የሚያሳዝነው አብረው ስለሚጨፈለቁት ቅዱሳን ሁሉ ነውይላል ቁጥ 12 ና 13 ምህረት ማድረግ የሚችለው አምላካችን ልቦናችንን አብርቶ ሀገራችንን ይፈውስ ህዝባችንን ይፈውስልን!!ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 14. Wow Daniel betkikil sirawun sertual malet new tengebegebachihu haratkawoch. Des sil endih sitchesu mayet

  ReplyDelete
 15. Ewunetun siyawuk hizib akatelachew enji ante endemitkebatrew Dani asgedido alakatelachewum. Wedaje kewedeku behuala menferaget lemelalat new seken bel.

  ReplyDelete
 16. ሐመርን ተቃጥላ ነበር ዱሮ አባ ጎረጎሪዎስ የጻፉዋቸውን መጽሀፍት እንዲሁ ተቃጥለው ነበር አቃጣዮቹ ስለጠቃጠሉ አቃጠሉ ግን ድጋሚ ታተሙ አሁንም ይታተማሉ ሲዲ ቢቃጠል ሲዲ ነው አገልግሎቱ ያበቃ ከ2 አመት በላይ የሆነው ዋጋ የለውም ግን በጣም የማከብረው ሰው ምን ነካው እውነት እየተመራመረ ነው ወይስ እየተመረመረ አረ እባክህ በጣም ወረድክክክ አታሳፍረን ትምህርት አስተምር ጊዜህን ስህተቶችን በማብራራት አቅምህን ተጠቀም ሰዎችን አትመልከት ለማህበር አትወግን አምልክን ውለታውን አስታውስ አሚሊዎን ሰዲዎች ታትመዋል አትደርስበትም እንዲሁም ዩቱቭ ውሎ ይግባ ሞልቶዋል ብዙ መሀይም፡፡

  ReplyDelete
 17. ወጣም ወረደም በዚህም አላችሁ በዚያ አሁንም እነሱ ሰርተው የሰጡትን ግጥም እና ዜማ ነው የምትሰሙ።የእግዚአብሄርን ቃል አይታሰርም።

  ReplyDelete
 18. Wow Dani Congra that should be done

  ReplyDelete
 19. ስራ የፈታ መለኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል!!!!!!

  ReplyDelete