Sunday, September 17, 2017

ቀሲስ ዘማሪ አሸናፊ ገብረ ማርያም ለጳጳሳቱ ይናገራል

ለጰጳሳት የተላከ ደብዳቤ ክፍል አንድ /ከቀሲስ ዘማሪ አሸናፊ /ማርያም/

ከፍ ያለ አክብሮት ለብጽዕናችሁ አቀርባለሁ፡፡ ወደዚህ ከፍ ያለ ጥሪ ስትመጡ ብዙ የህይወት ተጋደሎ አድርጋችሁ፣ በጠበበው ደጅ በትዕግስት ተራምዳችሁ ነውና መደመጥ ይገባችኋል፡፡ የደብዳቤዬ ዓላማ የእናንተ እረኝነት በትውልዱ ውስጥ ትርጉም ያለው ሆኖ እንዲቀጥል ያለኝኝ የልጅነት ናፍቆቴን ለማሳየት ነው፡፡ እናንተ የተቀደሰውን ህዝብ እንድትጠብቁ በእግዚአብሔር የተሾማችሁ እረኞች እንደመሆናችሁ ከፍ ያለ ክብር ይገባችኋል፡፡ በገዛ ደሙ የዋጃትን ቤተክርስቲያን ለመምራት የክርስቶስ እንደራሴ ናችሁ፡፡ ባለአደራ ናችሁ፡፡ የሐ፤ 2028 በሲመታችሁ ዕለት የምትገቡት ኪዳን እሳት ውስጥ ቀልጦ ለመጤስ እንደተዘገነ ቅዱስ እጣን ያደርጋችኋል፡፡ የሚቀጣጠል የመብራት መቅረዝ እጃችሁ ውስጥ አለ፡፡ ዘይቱን እየቀዳችሁ እስከ ሙሽራው መምጫ የምታበሩልን አምስቱ ልባሞች ናችሁ፡፡ በደብተራ ሙሴ ሃያ አራት ሰዓት ትበራ የነበረችውን ያችን መብራት አስቧት፡፡ መብራቷ ከጠፋች የእግዚአብሔር ክብር እንደ ጎደለ ማመልከቻ ነበረ፡፡ አፍኒንና ፊንሃስም መብራቱን በማጥፋታቸው ይወቀሱ ነበር ፡፡ 1 ሳሙ 33 

በእናንተ ልብ ውስጥ እረፍት የሚነሳ መብራት መቀጣጠል አለበት፡፡ ፍጥነታችሁ እንደ ቤተክህነት ሳይሆን መሬት ላይ እንዳለችው ዓለም መሆን አለበት፡፡ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ከአይሁድ ጋር እንደ አይሁድ ከአህዛብ ጋር እንደ አህዛብ ሆናችሁ መስራት አለባችሁ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጳጳሳት ይመገባሉ? ይተኛሉ? ይስቃሉ? ብለው በመገረም የሚጠይቁት በእነሱ ዓለም እንደምትገኙ ባለመረዳታቸው ነው፡፡ ጳጳስ ወንጌል አያስተምረም? ለመንጋው ሲል አይሞትም? ለኢየሱስ ክርስቶስ ደፍሮ አይመሰክርም? ብለው ነው መገረም ያለባቸው፡፡ እንደ ማንኛውም ህዝብ ቀለል ያለ ኑሮ የመኖር ነጻነታችሁን ጥሪያችሁ ወስዶባችኋል፡፡ በእጃችሁ ያለው መስቀል ስለክርስቶስ ሁሉን እንድትተውና ብዙ ዋጋ እንድትከፍሉ የኪዳን ምልክት ነው፡፡ 

አባቶቼ፡- ጌታ ለእረኛው ጴጥሮስ ኃላፊነት ሲሰጠው ታፈቅረኛለህ/በግሪኩ መጽሐፍ እንደሚለው/? ብሎ ነው፡፡ ዮሐ 2115 ጳጳስ አፍቃሪ ነው፡፡ ጌታውንም ሰውን የሚወድ፡፡ ጌታውን ሲወድ ሌላ ዓለም አይኖረውም፡፡ በጎቹን ሲወድ ይሞትላቸዋል፡፡ በውስጣችሁ ይህ ስሜት ከፍ ያለ ነው ወይስ ቀለል ያለ? ጌታችን በጎቹን፣ ጠቦቶቹን እና ግልገሎቹን እንድትጠብቁ አደራ ሰጠ፡፡ ይህ ማለት ጳጳሱ በጎቹን ለመጠበቅ ወርዶ የመንጋውን ስነልቦና በሚገባ ሊረዳ ይገባል ማለት ነው፡፡ በጎቹ ትላልቅ ምዕመናን ናቸው፡፡ አኒህ በጎች የዋህና አማኞች ናቸው፡፡ ብዙዎቹ በቂ መንፈሳዊ እውቀት የላቸውም፡፡ ማንም ሰው እንደፈለገ እንዳይነዳቸው ለብቻቸው የተጠና ትምህርት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በገንዘባቸው ዋና የቤተክርስቲያን መጋቢዎች ናቸው፡፡ የሚሰጡትን ያህል ከቤተክርስቲያን መቀበል አለባቸው፡፡የሚሰበሰቡባቸው መቅደሶች፣ የሚቀመጡባቸው ወንበሮች፣ ሃሳባቸውን የሚገልጡባቸው መድረኮች፣ ስለሞተላቸው ተምረው የጌታን ሥጋና ደም የሚቀበሉባቸውን እድል እረኛው ሊያዘጋጅላቸው ይገባል፡፡ ለምለም መስክ ላይ ማረፍ አለባቸው፡፡ በእርግጥ ጳጳሳት አብዛኛው በዚህ ዕድሜ ያሉትን አማኞች ለመረዳት አትቸገሩም፡፡ 

ጠቦቶቹ ወጣቶች - ወጣት እውቀቱ በየዘመኑ ስለሚያድግ ጠያቂና ተመራማሪ ነው፡፡ ወጣት በአመክንዮ ያምናል፡፡ እምነቱንና ስርዓቱን በአመክንዮ አስደግፎ መጓዝ ይፈልጋል፡፡ በመረጃ ዘመን እንደመገኘቱ ለተለያዩ አዳዲስ አስተሳሰቦች ተጋላጭ ነው፡፡ በጥንቃቄ ካልተያዘ አክራሪና ጽንፈኛ ሆኖ ቤተክርስቲያንን ወደ ኋላ ሊጎትታት ይችላል፡፡ ደግሞም ብዙ ጥያቄዎች አሉት፡፡ ግን ብዙ የማይፈሩ የተማሩ መላሾች ያስፈልጉታል፡፡ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ጥያቄ የማይፈራ መምህር መብዛት አለበት፡፡ ሃይማኖታዊና ፍልስፍናዊ ሙግቶችን መቋቋም የሚያስችል እውቀት መዳበር አለበት፡፡ ወጣት ስሜታዊ ሙግት ይወዳል፡፡ እምነቱ ሲገባው ዋጋ ለመክፈል ወደ ኋላ እንደማይል ሊቢያ በረሃ ውስጥ አይተነዋል፡፡ ስለዚህ የጠቦቶቹን እውቀት፣ ስነልቦናና ግንዛቤ ከግምት ያስገባ ደግሞም ከፍ ያለ እውቀት ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ በየቀኑ ጠቦቶቹን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሰንበት ትምህርት ቤት የሚሰበሰቡ ጥቂት ወጣቶችን እንዲሁም ቤተክርስቲያን ያልመጡ ሚልየን ወጣቶች ፍላጎት ምንድነው ብሎ መጠየቅ ይኖርባችኋል፡፡ ከተራራው በወረደ ጊዜ ብዙ ህዝብ ተከተሉት ተብሎ የተጻፈው ከቤተክርስቲያን ውጭ ያሉ ወጣቶች ከተሳላሚዎቹ እንደሚበልጡ ለማሳየት ነው፡፡ ማቴ 81

አባቶቼ፤- በኢትዮጵያ ሦስት አይነት ወጣቶች ተፈጥረዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ የገጠር ወጣቶች ናቸው፡፡ ለባህል ለሃይማኖታዊ ልምምዶች ምቹ የሆኑ ናቸው፡፡ ቃለ ምዕዳን የሚያዳምጡና የሚያከብሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዳንዶቹ በአምልኮ ባእድ እና ኃላ ቀር በሆኑ ልማዶች የታሰሩም ናቸው፡፡ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ የአንድ ብሔር እምነት ናት የሚሏቸው አባባዮችም ይረብሿቸዋል፡፡ አሁን አሁን በራሳቸው ቋንቋ ተምረው ስለሚያድጉ የሁላችሁንም ጳጳሳት ቋንቋ መስማት የሚችሉት ጥቂት ናቸው፡፡ 

ሁለተኛዎቹ የከተማ መካከለኛ ቤተሰብ ልጆች ናቸው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ትምህርትን፣ ዘመናዊነትንና ሃይማኖትን አዛምደው የሚኖሩ ቀላል በሆነ መንገድ መማር የለመዱ፣ ዲሞክራት የሆኑ በሚገባ የሚንከባከብ ወላጅ ያላቸው ናቸው፡፡ ተማሪዎቹ መምህራኖቻቸውን እየገመገሙ ያደጉ ናቸው፡፡ እኒህ ወጣቶች ከጳጳሳት የሚጠብቁት በዚሁ ልክ ነው፡፡ ለምን ብለው ሲጠይቁ መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ሙሉ መልስ ባላት ትልቅ ቤተክርስቲያን ውስጥ አንተ ጥያቄህ አላማረኝም ጀርባህ ይጠና መባል የለባቸውም፡፡ ቢሳሳቱም እንደ እናታቸው ቤት መታረም አለባቸው፡፡ ምክንያቱም የቱም ልጅ በቤቱ ተሳስቶ ታርሞ ነው ያደገው፡፡ የህይወት አመክንዮ በማይደግፈው መንገድ ስህተት አግኝቼብሃለሁና ውጣ! ሲባሉ ቤተክርስያን እናታችን አይደለችም ማለት ነው ይላሉ፡፡ አስተዳደሩ አልተመቸንም ይስተካከል ሊሉ ይችላሉ፡፡ ዛሬ በየአጥቢያው የሚነሱ ችግሮችና ፍትጊያዎች እረኞቻቸውን መገምገም በሚፈልጉ ጠቦቶች የሚፈጠሩ ናቸው፡፡ እረኛው ራሱን ለመፈተሽ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ እኒህን በፍቅር እና በብቃት የመምራት አቅማችሁን ማሳደግ አለባችሁ፡፡ እንደ ቴክኖሎጂ የወጣቶቹ አእምሮ በየጊዜው አብዴት/ይመጥቃል/ይሆናል፡፡ ስለዚህ እረኛውም በፍጥነት ራሱን አብዴት ማድረግ አለበት፡፡ ብዙ ማንበብ፣ በወጣቶች ስነልቡና ላይ የተጻፉ ጽሑፎችን መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ወጣቶች ፍቅር ሲያጡ እንደጠፋው ልጅ ድርሻዬን ስጠኝና ልሂድ ሊሉም ይችላሉ፡፡ ወደ ሌላ ቤተእምነት የሚጎርፉት ሳይመቻቸው ሲቀርና ሲረሱ ነው፡፡ መምህራኖቻቸውን መገምገም ለምደው ፍትህ ሲጎድል፣ ፍርድ ሲጠፋ ይናጣሉ፡፡ ጉባኤቸው ሲዘጋ፣ በሆነ ባልሆነው ምክንያት ሰንበት ትምህርት ቤታቸው ሲፈርስ፣ መዝሙራቸው ሲቃጠል፣ አስተማሪዎቻቸው ሲሰደዱ፣ አውደምህረታቸው በስድብና በርግማን ሲሞላ ከልባቸው ይመረራሉ፡፡ ይሸፍታሉ፡፡ ከወጡ በኋላም ወደ ሌላ ቤተእምነት ገብተው የቤተክርስቲያንን ርስት እየሸነሸኑ ለሰው ይሰጣሉ፡፡ እረኛው መሃላቸው እንደአባት ካልቆመ እርስ በርስ በሚፈጥሩት ፍትጊያ ይጨካከናሉ፡፡

የጠፋው ልጅ ሲመለስ ትልቁ ወንድም ለምን ገባ? ለምን ተመለሰ? እርሱ ካልወጣ አልገባም ብሎ ከደጅ ቆመ፡፡ አባታቸው ግን ደግ አሳዳሪ ነበር፡፡ ግባ ቤቴ ለሁለታችሁም ይበቃል ብሎ አብረው በፍቅር እንዲያድሩ አደረገ፡፡ እናንተም ይህን ማድረግ አለባችሁ፡፡ ትልቁ ልጅ ወደ መኖሪያችሁ መጥቶ ታናሼ ገንዘቡን በትኗል፣ አጥፍቷልና በርህን ዝጋበት፣ አውግዘህ ከቤተክርስቲያን ለየው፣ ሲላችሁ አይ ቤታችን ለሁለታችሁም ይበቃል ማለት አለባችሁ፡፡ ቀንድ ያለውን በግ ፈርቶ ቀንድ የሌለውን ጠቦት በአውሬ የሚያስበላ እረኛ እንዳትሆኑ መጠንቀቅ አለባችሁ፡፡ ሉቃ 1532

ዛሬ በቤተክርስቲያን በትላልቅ ወንድሞች የሚደረገው ዘርን የማጥፋት ሥራ ያለምንም ከልካይ የቀጠለው ጳጳሳቱ ልል ስለሆናችሁ ነው፡፡ ወደ ፊት ቤተክርስቲያንን ብዙ ዋጋ ያስከፍላታል፡፡ በሌሎች ቤተእምነት የቲቪ ቻናሎች የዳናችሁ ግቡ እያሉ ብዙ ኦርቶዶክስ ወጣቶችን ሲማርኩ በእናንተ ሚዲያ እከሌን አውጥቼ ጥየዋለሁ ብላችሁ ማወጅ ልክ አልነበረም፡፡ ፍቅር የእረኝነት ሃይል ነው፡፡ ፍቅር ከእምነት ይበልጣል፡፡ 1 ቆሮ 1313 የትኛውንም ወላጅ ጠይቁ፡፡ የወለደውን ልጅ ለአውሬ የሚሰጥ የለም፡፡ ይቀጣው ይሆናል እንጂ፡፡ በር ዘግቶ በጨለማ ውስጥ ለአራዊትአይተወውም፡፡ አባቶቼ ይህን ለማወቅ መውለድ አይጠበቅባችሁም፡፡ ልጅ በመውለዴ ይህን ደፍሬ እናገራለሁ፡- አባት አይጥልም! የወለደ በፍጹም አይጥልም! በአደባባይ አውግዤአለሁ የምትል ቤተክርስቲን የእኛ ናት፡፡ እንደ ቀድሞዎቹ አባቶች ጠርታ ሳታስተምር፣ ሳትጠይቅ ሳትመክር ውጣልኝ ማለት ሃብታም ነኝ ምን ይጎድለኛል ማለት ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ቢወገዝ አንድ ሳር ከሳር ቤት እንደተመዘዘ ነው የሚቆጠረው ምን ይጎዳል ያለች እስኪመስል መጨከን የለባችሁም፡፡ በእምነት ለተመለከተው አንድ ሰው አንድ ሺህ ነው፡፡ እግዜርም እንዲህ ነው የሚያየው፡፡ ከአንድ ሰው ጀርባ የሚመሰረተው ቤተሰብ ምን ያህል እንደሚሰፋ ታውቃላለችሁ፡፡ እንደ አዳም አሻግራችሁ ካያችሁ ካጠፋችው ሄዋን ጀርባ ህያዋን ዘሮች አሉ፡፡ አንድን ሰው ሳይንቁ ጠርቶ መምከር ሃሳቡን መጠየቅ ሺዎችን ማትረፍ ነው፡፡ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሲጠራ ደግሞ ዘንድሮ ማን ይወገዝ ይሆን? መባል እየተለመደ መጥቷል፡፡ እናንተ በሲኖዶስ ስትሰበሰቡ ማንን ያተርፉ ይሆን? መባል ነበረባችሁ! ልጆቻችሁ በናፍቆት ሊጠብቁ በፍቅር ውሳኔአችሁን ሊሰሙ ይገባል፡፡ በእውነት ተወዳጅ እንጅ አስፈሪ ሲኖዶስ መሆን የለባችሁም፡፡ አባቶች የዋሆች ናቸው ግን እነከሌ ይጠመዝዟቸዋል ለምን ትባላላችሁ? እናንተ ከሃገራችን መሪዎች የበለጠ ልዕልና ያለው ስልጣን አላችሁ፡፡ በትክክልም ማሰር መፍታት ትችላላችሁ፡፡ ግን ብዙ ጊዜአችሁን በመፍታት ማሳለፍ አለባችሁ፡፡ይስሃቅና ርብቃ ልጆቻቸውን ተከፋፍለው ስለወደዱ በሁለት ወገን መካከል ጠላትነትን አኖሩ፡፡ ፍቅር ታናሽ ታላቅ የለውም እኩል ነው፡፡ የሁለት ወገን አባት መሆናችሁን ልታሳዩ ይገባል ፡፡ እንደ ግብጽ ቤተክርስቲያን አስር ሚሊየን ስንደርስ መባነን የለብንም፡፡ 

ሃገር በራዕይ ይመራል ብለዋል ታቦ እምቤኪ፡፡ የነገዋን ቤተክርስቲያን በራዕይ መምራት አለባችሁ፡፡ መመልከት አለባችሁ፡፡ ነገ ጠንካራና ተወዳዳሪ ቤተክርስቲያን እንድትኖረን መቀነስ ሳይሆን መጨመር ነው የሚገባን፡፡ ትምህርታችንን መዝሙራችንንና ንግግራችንን ሌሎች ቤተእምነቶች ተደብቀው ወይ በግልጥ ሊማሩበት ካልሰሙ አልሰራንም ማለት ነው!!!!! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ወጣቶች ጳጳሳቶቻቸውን አባታችን ብለው ይጠራሉ፡፡ እንደ ጨዋ ልጅ ጉልበት ይስማሉ፡፡ በገዛ ቤታቸው በእንክብካቤ ስላደጉ ጳጳሳቸው እንዲንከባከባቸው ይፈልጋሉ፡፡ ይህን ጠቦት በሃይልና በማስፈራራት መግዛት የወጣቶችን ልብ ያስኮበልላል፡፡ የንጉስ ሰሎሞን ልጅ ሮብዓም እስራኤልን እንዴት እንደሚመራ ከሽማግሌዎችና ከጎረምሶች በተራ ምክር ጠየቀ፡፡ ከሽማግሌዎች ይልቅ የጎረምሶቹን "በሃይል ግዛቸው" ምክር ተቀበለ፡፡ በዚህ ኃይለኝነቱ እስራኤል ለሁለት ተከፈለች፡፡ እናንተም ከሽማግሎችም ጋር መምከር አለባችሁ፡፡ ጎረምሶች ለስህተት የሚዳርግ ሃይለኛ ምክር ያመጡላችኋልና፡፡ 2 ዜና 10 14 

ደግሞም ከደርግ ፓለቲካ ብዙ ልንማር ይገባል፡፡ ደርግ ትናንሽ አመጾችን ቀለል አድርጎ ይመለከት ነበር፡፡ ህውሓት ትንሽ ተገንጣይ ቡድን ነች ምን ታመጣለች እያለ ንቋት ነበር፡፡ ችግሮቻቸውን ከማዳመጥ ይልቅ በሃይል ልደምስስ ብሎ ትልቅ ሰራዊት አሰለፈ፡፡ ነገር ግን ተሸነፈ፡፡ ለትንንሽ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ መወያየትና ማወያየት ይገባል፡፡ የአንድ ቡድን አስተሳሰብ አራማጅ ብቻ ትክክል ነው የሌላው ጥያቄ ተራ ነው ማለት በመሳሪያ የማይመልሱትን እሳት ነው የሚጭረው፡፡ የወጣቶችንም የመታዘዝ መንፈስ ያጠፋል፡፡ከጥቂት ዓመታት በፊት በአንድ ከተማ መንፈሳዊ ትምህርት የሚማሩ ወጣች ነበሩ፡፡ መምህራቸው ክርስቶስን እንዲያከብሩ፣ ቤተክርስቲያንን እና አባቶችን እንዲወዱ ጠንካራ ትምህርት ሰጥቷቸዋል፡፡ ልጆቹም ይህን ተቀብለው ሲኖሩ ሳለ ሊቀጳጳሱ መጥተው በአንድ አወዛጋቢ ጉዳይ ፍትሃዊ ያልሆነ ውሳኔ በስሜት ወስነው ወደ መጡበት ተመለሱ፡፡ ከወጣቶቹ አንዱ ሼም ለስ ጳጳስ! አለ፡፡ መምህሩ እንዴት እንደዚህ ትላለህ ብሎ ተቆጣው፡፡ አዎ ልክ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን እንደዚህ አንዳልል አባቴ ሊያግዙኝ ይገባ ነበር አለ፡፡ አያችሁ፡- የጠቦቶቹ መታዘዝ ከእናንተ ፍቅርና አስተዋይነት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ?! 

ትውልዱ በከፍተኛ ደረጃ የማወቅ ፍላጎቱ ጨምሯል፡፡ እራሳችሁን ለትውልዱ ጥያቂ መልስ ሰጪነት ልታዘጋጁ ይገባል፡፡ እውቀታችሁ ተጠያቂ እስኪያደርጋችሁ ድረስ ማደግ አለበት፡፡ ቤታችሁ ውስጥ መንፈሳዊና ዘመናዊ መጽሐፍት በትልቅ ሼልፍ ተደርድረው መቀመጥ አለባቸው፡፡ እውቀት ከመንፈሳዊነት ጋር ከሰፋ አጠፋ የተባለን ሰው ጠርቶ፣ አናግሮ፣ መስመር ማስገባትና ማደላደል አይከብድም፡፡
ደግሞም ወደ ሰው ጠጋ ማለት አለባችሁ፡፡ ታች ባለው ህዝብና በእናንተ መሃል ያለውን ክፍተት መካከለኛ ሰዎች ከገቡበት ያሳስቷችኋል፡፡ እነርሱን ጥሳችሁ ወደ ታች ውረዱ፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ወደ አዲስ አበባ በመጡ ሰዓት እሁድ ቦሌ መድሃኒዓለም ሊያስቀድሱ መጥተው ሳለ እናንተና የግብጽ ጳጳሳት በብዛት ተገኝታችሁ ነበር፡፡ በዛን እለት የእኛ አባቶች በቅድስት ውስጥ ቆማችሁ ሳለ የግብጾቹ ጳጳሳት ግን ሕዝቡ ውስጥ እየተዘዋወሩ ፎቶ እያነሱ፣ እየጨበጡ፣ እያሳለሙ ነበር፡፡ በርግጥ የአኗኗር ዘይቤአችን የተለያየ እንደሆነ ግልጥ ነው፡፡ነገር ግን እረኛ በግ ተራ ሲወርድ ደስ ይላል፡፡ ቀለል ያለ አቀራረብ ሰው ልብ ውስጥ በተለይ ወጣቶች ልብ ውስጥ እንድትገቡ ያግዛችኋል፡፡ 

ሦስተኛዎቹ ዘመናዊ እና የባለጠጋ ቤተሰብ ልጆች ናቸው፡፡ ጳጳሳት ከእነዚህ ልጆች ጋር ስትገኛኙ ምን ይሰማችኋል፡፡ ጸጉሩን በስታይል የፈሸነ፣ በጆሮው ሎቲ ያጠለቀ፣ ወረድ ያለ ሱሪ የለበሰ፣ አማርኛ የማይቀናው፣ ምናልባትም አሺሽና መጠጥ የለመደ፣ ቆዳው ሃበሻ ልቡ ግን ፈረንጅ የሆነ፣ ይህንንም እንደመብት የሚቆጥር ወጣት በአዲስቱ ባለጠጋ ኢትዮጵያ ብቅ ብሏል፡፡ ይህን ወጣት ለማስተማር አስባችሁት ታውቃለችሁ? በእርግጥ እኛ ለእንግዶች ማደሪያ ስፍራ አለን? እኒህ ዘመናውያን ሬጌውንና ሂፓፑን ትተው መዝሙር ልስማ ቢሉ ከተቃጠለው የተረፈ ማንን ነው የሚሰሙት? በዓውደ ምህረታችን ከተሜና መንፈሳዊ ሰባኪዎች አሉን? ቲዮሎጂና ሶሽዮሎጂ የተማረ የወጣቶች ጳጳስ ለምን አይኖረንም? 

ጳጳሳት የዚህ ትውልድ ባለአደራ ናችሁ፡፡ ስሜቱን ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡ ደጀ ጠኚ የቆሎ ተማሪዎችን ተገንዝባችሁ እንደምታገለግሏቸው እኒህን ሳትነቅፉ የመጠበቅ ኃላፊትአለባችሁ፡፡ ይህኛው ወጣት እንኳን ከእናንተ ከከተሜው ወጣት ጋርም ተግባብቶ ለማደር ይቸገራል፡፡ በአንድ የስፓርት ማዕከል ሻወር እየወሰድኩ ሳለ አጠገቤ ሃብታም ጎረምሳ ከተሜዎች እያወሩ ይታጠባሉ፡፡ እውነት ለመናገር ምን እያሉ እንደሆነ ለማወቅ አልቻልኩም፡፡ ቦከሰው፣ ከወደው፣ አረፈው በሚሉ ቃላት ነው የሚያወሩት፡፡ እንግዲህ ጌታ ጠቦቶቼን አደራ ያለው እኒህን ነው፡፡ ምን እያሉ ነው? ምን ያስፈልጋቸዋል? ማለት ግድ ነው፡፡ ስሜታቸውን እና ፍላጎታችውን ሳይናገሩ ከፊተቻው ማንበብ እና በመጠናቸው ማገዝ የእረኞች ሥራ ነው፡፡ የእነዚህን ወጣቶች ቀልብ የሚሥብ ሰባኪ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡

ግልገሎች ህጻናት ናቸው፡- ህጻናት ሁልጊዜ እንደምንለው የነገዋ ቤተክርስቲያን መኖር ማረጋገጫ ናቸው፡፡ እንክብካቤ ያልተለያቸው እና ጤነኛ ህጻናት በኢትዮጵያ ተፈጥረዋል፡፡ እነዚህ ህጻናት ዛሬ ከቤተክርስቲያን የሚያኙት ብቸኛ ነገር ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ መቸም ከሃያ ዓመት በላይ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከገጠር እስከ ከተማ ተዘዋውሬ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ጎብኝቻለሁ፡፡ በበዙት ሰንበት ትምርት ቤቶች የህጻናት ክፍሎች የሏቸውም፡፡ ቢኖሩም በጣም ጥቂትና ያልተደራጁ ናቸው፡፡ ማንፈጠረህ? የሎጥ ሚስት ማነው ስሟ? የማቱሳላ እህት ስሟ ማነው? በሚሉ ቀላል ትምህርቶች የተሞሉ ናቸው፡፡ ልጆቹ ከቤተክርስቲያን ከሚያገኙት ይልቅ በዓለማዊ ሚዲያዎች የሚማሩት በልጦ ተገኝቷል፡፡ ምዕራብ ሸዋ ውስጥ በሚገኝ በአንድ አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት መምህሩ ስለመጥምቁ ዮሐንስ አወላለድ እያስተማረ ሳለ በማህጸን የዘለልው ህጻን ማነው? ሲል አንድ ፊት የተቀመጠን ህጻን ጠየቀው፡፡ ልጁ የፊልም ሰዓት ደርሷል እያለ እያሰበ ነበርና ድንግጥ ብሎ ቻንድራ ! አለ፡፡ ብዙ ተሳቀ! ነገር ግን የዚህን ህጻን ልብ ወደ ቤተክርስቲያን የሚመልስ የተጠና ትምህርት ከላዘጋጀን እንደ አውሮፓውያን ቤተክርስቲያን የሽማግሌዎች ሆና መቅረቷ ነው፡፡ ዛሬ በአውሮፓ ቤተክርሰቲያን የሚሄዱት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተረፉ አረጋውን ናቸውና፡፡

ጳጳሳት አባቶቼ፤- በህጻናት ጉዳይ ላይ የሚሠሩ የህጻናት ጳጳስ መመደብ አለባችሁ፡፡ ጳጳሱ በእውቀት ላይ የተደገፈ መረጃ ያላቸው እና ወደ ሌላ ሃገረ ስብከት ቀይረው የማይሄዱ በቋሚነት የሚተጉ ሊሆኑ ይገባል፡፡ የተጠኑ ጽሑፎችን፣ ሲዲዎችን የሚያዘጋጅና የሚያሰራጭ የህጻናት መምሪያ ሊኖር ይገባል፡፡ ትውልድ የሚቀርጽ ራዕይ ያለው ሥራ ከተጀመረ ገንዘቡ እንደወንዝ ከምዕመናን ይፈሳል፡፡ ህዝባችን ገንዘብ ለመስጠት አሳማኝ ምክንያት ብቻ እንደሚፈልግ ታውቃላችሁ፡፡ 

የሃገራችን ህጻናት ጠቅላይ ሚኒስቴራችን እንዳሉት ዲሞክራት እና ንጹህ ናቸው! መዋሸት አይፈልጉም፣ ጭቆና አይፈልጉም፣ ዲክታተር አስተዳደር አይፈልጉም፣ ጥያቄ የማይመልስ አስተማሪ አይፈልጉም፣ ፈረንጅም ሃበሻም ናቸው፡፡ ከባድ የሚባለውን ትምህርት የሚገነዘቡ ባለ ክፍት አእምሮ ናቸው፡፡ የሚወዳቸውን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ጸጉር ሰሪያቸው እንኳ አመናጭቆ ካናገራቸው ተመልሰው ወደ እዚያ መሄድን የሚቃወሙ ናቸው፡፡ የነዚህን ነጻና ቅዱስ አእምሮ ሌሎች ቤተእምነቶች በሚያቀርቡላቸው ቀለል ያሉ ትምሀርቶች እንዳይወሰድ መባነን አለባችሁ፡፡

ቡራኬአችሁ ይድረሰኝ

ይቀጥላል
 
 (ጽሑፉ የተወሰደው ከጸሐፊው የፌስቡክ  ገጽ ላይ ነው)

16 comments:

 1. ጽሑፉ መካር ነበር ዳሩ ግን እስመ እም ተረፈ ልብ ይነብብ አፍ ማቴ 12/34--36
  ሰባኪዎቹ ካልታጣ መልካም ነገር የሚያስደነብር የሚያስወገሽ የሚያቅለሸልሽና የሚያቀርብ ሳይሆን የሚያሸሽ መርዝ ይረጫሉ መጽሐፍ (ከልብ ሞልቶ የተረፈውን አፍ ይነዘዋል)እንዳለ መድረኩ
  መናፍቃን ከሀድያን ሐሳውያን በሚሉ ቃላት ስለተሞላ ጥሩ ትምህርት ለማዳመጥ የመጣ ምእመን ይሰለቸውና እየጐፋ አቅጣጫውን ቀይሮ ይሄዳል። ሰባክያኑ ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ ጐረቤትህ ጤና ይደር አንተም ጤና እንድታድር የሚለውን ያገር ቤት አባባል ዘንግተዋል ባንደበት መልካምጂ ክፉ ሊናገሩበት አይገባም ነበር ዳሩ ግን ምን ይደርግ!ዐለም ለስደብ አፉ ተክፍቷልና ምእመናን ጥናቱን ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 2. endih ayinet tsihuf des yilal kalehiwot yasemalin  ReplyDelete
 3. ዓሸናፊ (ቀሲስ) ስመ ጥሩ መምሕር፡ ጉራጌ ዞን በወንጌል ብርሐን የለወጠ ታላቅ መምሕር ነው:: በተቃራኒው ስለ መምኅሩ የሚነዛው መሰረተቢስ ወሬ ተራ የመንደር አሉባልታ ነው፡፡

  ReplyDelete
 4. አሸናፊ (መምኅር) መንካት በቀጥታም ይሑን በተዘዋዋሪ ጉራጌ ዞን በእሳት እንደ ማቃጠል ነው፡፡ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል እና ቅድመያ ማስብ ተገቢም አስፈላጊም ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. አሸናፊ (ቄስ) መንካት ዋጋ ያስከፍላል፡፡

  ReplyDelete
 6. "ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ: በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተላለፈውን የፓትርያርኩን ኢ-ሲኖዶሳዊ እገዳ ውድቅ አደረጉ፤ስለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት አሳሰቧቸው". Who is priest in charge our church ? ስራስኪያጅ or The Patriarc? Writer knowledge is naive regarding to modern management chain of command. Please u f...idiot read more.

  ReplyDelete
 7. eshi mikru tiru nw betam miyasazinew gin mazenagia mehonu nw ...enante libe dendanoch byance ye thadso siltko ke indea and armenia bemigeba temrenal hulem yikrta teyiko memeles ena asmesaynetachu libonan yigezal gin yemezgiawn bret nwna yetekawemachut lenante yibsal enji mitfetru tamir yelem....betekristian zemenawi lemebal thiology yetemare abat yasfeligatal blo masebo yasaZNAL abnetu azeminen tiwlid enafrabet bihon bego milketa nbr gin zemenawinet lenante yerasin shito alemwan meslo menor nw...lastewayoch demo beras neger medmek yeras neger masadeg nw.

  ReplyDelete
 8. I just confused. Who is in charge Eotc? ማሕበራት: ስራስኪያጅ or Patriarc? The Patriarc is head of our church, CEO & President. All of you are responsible to answer him. Can you please respect chain of command? Otherwise you guys all of fight for power.

  ReplyDelete
  Replies
  1. No individual CEO is there in our church. rather who is in charge is the Holy synod. Hey, you men, it is different from that of you. The protestant/the so called tehadiso.

   Delete
 9. ማኅበረ ቅዱሳን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚቀሳቀሰው ድርጅት ለግንቦት ሰባት ዐሸባሪው ቡድን Eotc የሚሰልለት መሖኑና ፓትሪያርኩን ስራቸውን በማኮላሸት ውጤታማ ስራ መስራቱን በምስጢር ለግንቦት ሰባት የላከው ሪፖርት ያስረዳል።

  ReplyDelete
 10. ጳጳስ ተብዬው የኅጅ ኑርበግን ልጅ

  ReplyDelete
 11. ጳጳስ ተብዬው የኑበገን ልጅ

  ReplyDelete
 12. ጳጳስ ተብዬው የኑርበገን ልጅ ፩፰ ልጃ ገረዶች ደፍሮ ፩፮ ሲደቅሉለት ፪ መከኑበት። There is no moral power to blame or accuse ቀሲስ አሸናፊ። We all mk to our church. But not safe haven of mafiya such kind of none ethical priest.

  ReplyDelete
 13. ለቅዱሳን ያልተመለሳችሁ ለመላእክት ያልተመለሳችሁ ዘረኞች ደግሞ አሁን አለቀባችሁ እና ጉራጌን ለማስተባበር ተነሳችሁ:: አሸናፊ በሃይማኖቱ እንጂ በብሄሩ አይደለም ለኛ መመዘኛው:: ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ በምዕላት የሚወስነው ነገር የምንገዛበት መመሪያችን ነው::አሁን ፓትርያሬኩ ማህበረቅዱሳንን ስለጠሉ ብቻ ብደግፏቸው ቆይቶ ስለቅዱሳን በሚያስተምሩት መንቀፋችሁ አይቀሬነው:: እርሳቸው ያሰራር ጉዳይ እንጂ የሃይማኖት ችግር ያለባቸው አይመስለኝም እና ከእናንት ከጭለማ ልጆች ጋር አንድ እንዳይመስሉአችሁ:: እግዚአብሄር እውነቱነ ይግለጽላችሁ::

  ReplyDelete
 14. ጳጳስ ተብዬው የሐጅ ኑርበገን ልጅ በእናቱ ኤርትራዊ በአባቱ ስልጤ ነው። ማሕበረ ቅዱሳ ቆንጆ አሮጊት ስራ አጥ የማሕበሩ ሴቶች ለጳጳሳቱ መዝናኛ እንደ ሚያቀርብ ተጋለጠ።

  ReplyDelete
 15. "ቅዱስ ሲኖዶስ: በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ የ14 ቀናት ጸሎተ ምሕላ ያውጃል፤ ከመንግሥት ጋራ ይነጋገራል"what is this? Who is responsible for media , communication and public relations? The church has legal wright to file law suit. Because mk is not appointed by Eotc management to lead as press section of EOTC to release information for public regarding to EOTC.

  ReplyDelete