Monday, October 16, 2017

በትምህርት ሲያቅታቸው በጉልበት
የተሐድሶ እንቅስቃሴ ከጫፍ የደረሰ ይመስላል ጸረ ወንጌል ቡድኖች የወንጌል እውነት የተላለፈባቸውን መጻሕፍትና የመዝሙር ሲዲዎች ማቃጠል ይዘዋል ከዚህ ቀደም በሻሸመኔ አሁን ሰሞኑን ደግሞ በድሬዳዋ ይህን አስመልክቶ ኤልጃይስ የተባለ ወንድም በፌስ ቡክ የለጠፈውን ጽሁፍ እናስነብባችሁ፡፡

ይድረስ፤ ለተወደድከው ወንድማችን ዳንኤል ክብረት
Daniel Kibret Daniel Kibret Blog Daniel Kibret Views
ወንድማችን ዳንኤል ክብረት፤ ሰላምና ጤና በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለአንተ ይሁን፡፡ (ዳኒ፤ ዲያቆን፣ ሙሃዘ ጥበባት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብቸኛው ተመራማሪ የሚሉ የማዕረጋት ስያሜዎችህን መጠቀም ባለመፈለጌ፤ ከልብ ይቅርታ እጠይቅሃለሁ)፡፡ ዛሬ ስምህን እንድጠራ ያስገደድኝ ነገር ሰሞኑን በድሬደዋ የፈጸማችሁት አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ ለዚህችም አጭር ጡመራዬ ምላሽህን እጠብቃለሁ፡፡ አንተ የደራሲያን ማኅበራት ላይ አለው አለው የምትል ግለሰብ ስትሆን፤ የፈጸምከው ድርጊት በጣም አስተዛዛቢ ነው፡፡ ዳኒ አንተ እኮ ባገኘሁ ሚድያ ሁሉ፤ ለደራሲያን መብት እቆማለሁ፣ ለፕሬስ ነጻነት እሟገታለሁ የምትል ግለሰብ፤ እንዴት ባለ አዕምሯዊ እሳቤ ብትነሳ ነው የሰው አዕምሮ ውጤት የሆኑ ዝማሬዎችን፣ መጻሕፍትን፣ ስብከቶችን፣ ቪሲዲዎችን፣ የኅትመት ውጤቶችን በአደባባይ ለማቃጠል የተነሳኽውይህ በእውነት ከአንተ ይጠበቃል ዳኒ?


እውነት ነው ሰብስባችሁ ያለምንም ገላጋይ ያጋያችኋቸውን ዝማሬዎች፣ የኅትመት ውጤቶች፣ ቪሲዲዎችና መጻሐፍቶችን እንደማትቀበሏቸው የታወቀ ነው፡፡ ነገር ግን አንድን የኅትመት ውጤት ባለመቀበልና በመጥላት መሰረት ብቻ ቆሞ በአደባባይ እንዲህ አይነት አስነዋሪ ድርጊት መፈጸም ወንጀል እንጂ ጽድቅ አይደለም፡፡ የቀደሙ አባቶቻችንም ሐሰትን በእውነት ሲረቱ እንጂ እንደእናንተ አልተልፈሰፈሱም ነበር፡፡ ታሪካቸው ዛሬም ድረስ ለእኛ ሕያው ምስክር ሆኖ የቆመ ነው፡፡ እነ ቅዱስ አትናቴዎስ፣ እነ ቅዱስ ቄርሎስ፣ እነ ቅዱስ ኤጲፋኔዎስ፣ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  የሐሰት ትምህርትን እያሳደዱ በሰልፍ ለማጥፋት ሲባዝኑ ሳይሆን የምናውቃቸው በእውነት ቃል ሲረቱ ነው የምናውቃቸው፡፡ እናንተ ግን በእውነት ከየት ነው በቀላችሁበውኑ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እንዲህ አስተማረቻችሁንመንፈሳዊ አባቶቻችሁ እነማን ናቸውአዎን፤ በርግጥ አባታችሁ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ነው፡፡ የግብር አባታችሁ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ የቀደሙ አባቶቻችንን እነ ቅዱስ እስጢፋኖስንና ደቂቀ እስጢፋኖስን በእውነት ቃል ሳይሆን ሞግቶ የረታቸው በሰይፍ ነው ያስጨፈጨፋቸው፡፡ በእሳት ነው የገደላቸው፡፡ በንፍር ውሃ ነው የቀቀላቸው፡፡ ይገርምሃል፤ በስጋ ቢሞቱም የእነርሱ ልጆች ዛሬ ምድሪቷን ሞልተን ከድነናል እንጂ አንዳች ስንኳ አልጠፋንም፡፡ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ነገም እንበዛለን፡፡
ደግሞስ የአንድን አስተምህሮ ሥህተትና ምንፍቅና መከላከልና ማጥፋት የሚቻለው በዚህ ዓይነት አሳፋሪና የወረደ ድርጊት ነውንአዕምሯዊ አስተሳሰብን፣ ልባዊ እምነትን፣ በማቃጠል ሕግ በውኑ ማጥፋት ይቻላልንይህ ከንቱ ድካም መሆኑን ለማሳወቅ የግድ የሒትለርን ታሪክ ማስታወስ አይጠበቅብንም፡፡ ሐሰትን በእውነት ነው የምትረታው እንጂ በልፍስፍስ ግብር አይደለም፡፡ ክርስትናን በሰይፍ ለማጥፋት መሞከር የልፍስፍሶችና የደካማዎች መገለጫ ነው፡፡ አታስታውስም እንዴ ከክርስቶስ ዕርገት ማግስት በኋላ የተነሳው፣ ክርስትናን በሰይፍ ብዛት ለማጥፋት ብሎ የደከመውን ታላቁን ገዳይ ኒግሮን አታስታውስምይገርምሃል፤ ኒግሮ ሞቷል - ኢየሱስና የኢየሱስ ተከታዮች ግን ዛሬም ድረስ በድል አሉ፡፡ ምነው በየስፍራው የምታነሳቸው፤ የእነ ቅዱስ ቶማስ ዘመራስ ታሪክ በራሱ አዕምሮህ ላይ አይቃጭልምበውኑ ቶማስን የእጁ መቆረጥ ከክርስትና መለሰው እንዴየቶማስ እግር መቆረጥ ክርስቶስን ከመከተል አቆመው እንዴአላቆመውምምክንያቱም የክርስቶስ ሕይወት የታተመው በልባችን መቅዱስ እንጂ በእጅና በእግራችን ላይ ስላልሆነ ነው፡፡ ምናልባት ቶማስን ከክርስትና መመለስ የሚቻልበት መንገድ አንድ ነበር፤ እርሱም በልቡ ያከበረውን እውነት በመሞገትና በማሳመን ብቻ ነው፡፡ ቶማስ ግን ከሚያወጣው የእውነት ቃል የተነሳ የተቋቋመው አንዳች ሰው ስላልነበር ነው የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ወደ እግር ቆረጣ የገቡት፡፡ አንተም ‹‹ካሴትና ቪሲዲ›› ሰብስበህ በማቃጠል እውነትን ከቶ ልታጠፋው አትችልም፡፡ የኅትመት ውጤቶችን አቃጥለህ የምትለውጠው አንዳች ትርፍ አይኖርህምይሄን አንተም እኛም በሚመጡ ዘመናት እናያለን፡፡ ግን ለምን ይመስልሃል ክርስትና በሰልፍና በሰይፍ የማይጠፋውአየህ ዳኒ፤ ክርስትና የቆመው በክርስቶስ ላይ ስለሆነ፤ በስይፍ አታጠፋውም፣ በእሳት አታቃጥለውም፣ በንፍር ውሃ ቸልሰህ አታደፍነውምእውነት እውነት እልሃለሁ፤ እውነትን ማጥፋት አትችልም፡፡ ይሄን የልቤ ንጉስ በሆነው በጌታዬ በኢየሱስ ስም አረጋግጥልሃለሁ!
ጸጋና ሰላም ይብዛልህ!አክባሪህ ወንድም ኤልጃይስ!

8 comments:

 1. ወዳጄ ኤልጃይስ፡- አንተ ያልገባህ ወደፊትም ሊገባህ የሚከብድህ ነገር ተፈጸመ፡፡ በቃ፡፡
  አንዳንድ የዋሃን ትምህርቱን ሳይሆን የሰባኪውን/የዘማሪውን ድምጽና መልክ፣ ለሥጋ የሚመች የጭፈራ ዜማ አፍቅረው፣ በጣም ወደው የሰበሰቡትን ካሴት እንዲሁ በቀላል የሚጥሉ፤ የሚያቃጥሉስ ይመስልሃልን፤
  ይህንን ነው አልገባህም፣ አይገባህም ያልኩከህ፡፡ ያፈቀሩትን ለመተው የበለጠ ጉልበት ያስፈልጋል፡፡ አቅም ይጠይቃል፡፡ ሳይማሩ፣ አውቀትና መረጃ ጎድሎአቸው የያዙትን የሞት መንገድና ኮተት፣ ትክክለኛው ትምህርት ሲገባቸው፤ የሸረባችሁት ሴራ ጠርቶ ሲታያቸው፤ ባጠራቀሙት የሞት ፋይል ከራሳቸው አልፈው ትውልድ እንደሚገድሉ ሲገባቸው እኮ ነው የጣሉት፣ ያቃጠሉት፡፡
  ይህንን ኃይልና ብቃት ባያገኙ አያደርጉትም፡፡ ይህ ደግሞ በአንድ ቀን የጉባኤ ስብከት የሆነ መስሎህ ከሆነም በቃ አንተ አይገባህም፡፡ ለረዥም ጊዜ ቅድስት ቤ/ክ የምታስተምራቸውን እኽ ብለው ሲሰሙ ቆይተው የሞት ጦማሮችን ያቃጠሉበት ቀን እኮ የመጨረሻ የቀብራችሁ ቀን ነው፡፡ ከቀብር በፊት የነበረውን የማስታመም፣ ሲሞትም የዕድር ጥሪ፣ የንፍሮ መቀቀል፣ የመቃብር ቁፈራ፣ ወዘተ ጊዚያት ረሳሃቸው እንዴ፤
  የሚያስቀው ሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤልን በፕሬስ መብት፣ ወዘተ ለማሸማቀቅ መሞከርህ ነው፡፡ እርሱ ብዙ ነፍስ የሚያድንበት ሥራ ስላለው ላንተ መልስ በመጻፍ ጊዜ አያጠፋም እንጂ፣ እስኪያቅርህ ያጠጣሃል፡፡

  ኃይለሥላሴ ነኝ ከመሃል ሀገር

  ReplyDelete
  Replies
  1. Halesilassie, Selam Yihunilih!

   Who is your "Amlak" up on whom you have "hope"?. . . Do not tell me (or your self ) it is "EgziAbher". Please look where you are fallen.

   Your statement says a lot about that you don't know GOD (The Father the Son and the Holy Spirit).. ."Ke Fireyachew Tawquwachewalachu Teblo Enedetetsafew". Ke Egziabher yehonuna Egiziabherin Tesfa Yemiyadergu kifu'na Yemayanits neger aynagerum.

   May Holy Spirit show you the way,so that You may turn to and be saved by Our Lord Jesus Christ, and Get Mercy from God our Father.

   Then You will definitely have eternal hope in Trinity (God the Father, the Son and the Holy Spirit).

   Sincerely Yours,

   Rosa negn Ke Dar Ager.

   Delete
  2. አትድከም ወንድሜ ለጥፋት የተዘጋጀ ሰው ምንም እውነት ቢነገረው አይሰማም

   Delete
 2. አይ መልስ !!! እንዲሀ ንገርልኝ እነጂ!!! ፡፡አልታየህም ሙአዘ ጥበባት ስራ ፈትቶ ለርሱ መልስ ሲሰጥ፡፡ ጀግኖች ተራራውን ከናዱት ደልድሎ ሜዳ ለማድረጉ እኛ ህጻናት እንበቃለን በለው፡፡ ይልቅ እልህ መጋባቱን ትተህ የተሰጠህን የንስሀ ጊዜ ተጠቀምበት፡፡

  ReplyDelete
 3. ሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ላንተ የሰፈር አሉባልታ ግዜ የለውም። መናፍቅ!

  ReplyDelete
 4. እውነቱ ይነገርNovember 8, 2017 at 4:56 AM

  ውድ ኃይለ ስላሴ?

  መጠሪያ አድርገህ እየተጠቀምክበት ያለው የስላሴ ኃይል በሚገለጥበት በዚያቀን እንደዚህ ያለ ቆንጆ የአማርኛ ጽሑፍ አክሮባት ምክንያት ጌታ የሚቀበል ቢሆን ኖሮ እውነትን ጉድ አድርገሃት ነበር!ግን ለስሙ አጠራር ክብር ይሁንለትና እውነት ራሱ ጌታ ኢየሱስ ስለሆነ እውነትን ማቃጠል አይደለም ገላችሁ ብትቀብሩትና ለመቃብሩ ጠባቂ ብታስቀምጡም በስላሴ ኃይል ከሞት መነሳቱን በፍጹ አታስቀሩትም!የምናመልከው አምላክ ኢየሱስ መቃብር ያላያዘው የትንሳኤ ጌታ ነውና፤
  ስለዚህ እናንተም አይደለም የሥራ ውጤቶቻችንን እኛንም እንደ 3ቱ ደቂቅ በሰባት እጥፍ ብታቃጣሉን አሁንም ለጣኦት በምንም መልኩ አንሰግድም!!!

  ReplyDelete
 5. Can you explain me why you ignore my comment regarding with Haile Selasie idea please???

  Eunetu yeneger

  ReplyDelete
 6. እንዴ የተወደድክ ወንድሜ ዕራሱ በጋሻው እኮ የውሸት ትምህርቶች ነበር ያስተማርኩት መንፋስ ቅዱስ አልገለጹልኝም አለ አልሰማህም እንዴ? እንዴት ነው ዳንኤልን ተጠያቂ የምታደርገው? አሁን ግዜው እውነት የምትገለፅበት ነው እውነት ደግም አርነት ታወጣለች,እውነት እየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለጠፈትም በውነት ወደልባቸው እንዲመለሱ እንፀልያለን የድንግል ምልጃ ይጠብቃቸው። አሜን!!!

  ReplyDelete