ስለ አባ ሰላማ ብሎግ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
አባ ሰላማ ወይም ፍሬ ምናጦስ፤ ከሳቴ ብርሃን እየተባሉ የሚጠሩት አባት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ  ሲሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ታላቅ ዕድገት ያደረሱ ባለውለታ አባታችን ናቸው። ይህች ብሎግ የእርሳቸው መታሰቢያ ትሁንልን።
ይህች ብሎግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተ ክርስቲያን እየተባባሱ የመጡ አመጻዎችን፣ ክህደቶችና የስሕተት ትምህርቶችን፣ በማጋለጥ ማስጠንቀቂያዎችንና ትምህርቶችን ለመስጠት የተዘጋጀች ናት።
እንዲሁም በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተነሡ ሁለት ኃያላን እነርሱም ማህበረ ቅዱሳን እና ቤተ ክርስቲያናችን ተሃድሶ[መሻሻል] ያስፈልጋታል የሚሉ ወገኖች የሚወያዩባት ነጻ መድረክ ናት። በዚህች መድረግ የሰውን ስም ከማጥፋት እና ከስድብ ነጻ በሆነ ሥነ ጽሑፋዊ ጨዋነት መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት ይቻላል። የግለሰብን ስም ያለ እውነተኛ መረጃ በመጥፎ የሚያነሱ ሥነ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ብሎጓ ፈጽሞ አትቀበልም።
ብሎጓ የሁለቱን ሐሳቦች እና አመለካከቶች ከመጽሔቶቻቸው፤ ከመጻሕፍቶቻቸው እና ከስብከቶቻቸው ታቀርባለች። እንዲሁም ወቅታዊ እና ትኩስ የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ዜናዎችንም ትዘግባለች።
ይህን የውይይት መድረክ የከፍትንበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያናችን ምእመን በተባራሪ ወሬዎች ግራ ሳይጋባ ሁሉንም በውል ተረድቶ የሚጠቅመውን እንዲይዝ ራሱንም ከወንበዴዎች እንዲጠብቅ ለመርዳት ነው። እውነተኛ ላልሆኑ መረጃዎች አባ ሰላማ ኃላፊነት አትወስድም። እግዚአብሔር አይለየን!